ዶ/ር ዳንኤል በቀለ፤ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር ሆነው የተሾሙት ሰኔ 25 ቀን 2011 በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሁንታ ነው፡፡
የሕግ ባለሙያና የሰብ ዓዊ መብቶች ተሟጓች የነበሩት ዳንኤል በቀለ፤ ቀደም ሲልም የሰብዓዊ መብቶች ተመልካች ድርጅት የአፍሪካ ቅርንጫፍ ዳይሬክተር ሆነው ሠርተዋል።
በዓለም አቀፍ ሕግ ሶስተኛ ዲግሪያቸውን እንዲሁም በዓለም አቀፍ ሕግ ሰብዓዊ መብቶች ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ያገኙት ከእንግሊዝ ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ሲሆን፤ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በማኅበራዊና የአካባቢያዊ ልማት የተቀበሉት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነው።