"አዲሱ ዓመት ትኩረታችን፣አንደበታችንና አቅማችን በሙሉ ስለ ግድያና ሞት ሳይሆን፤ስለ ልማትና ዕድገት የምናስብበትና የምንሠራበት እንዲሆን እመኛለሁ" አምባሳደር ሃደራ አበራ

Ambassador Hadera Abera Admasu I.jpg

Hadera Abera Admasu, Ethiopian Ambassador to Australia. Credit: Embassy of Ethiopia, Canberra

በአውስትራሊያ የኢትዮጵያ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሃደራ አበራ "በዓሉን በደስታ ለማክበር ስታስቡ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ፤ አገር ቤት የሚገኙ ቤተሰቦቻችሁ ሰላምና ደህንነት እንደሚያሳስባችሁ፤ የትውልድ አገራችሁ ዕጣ ፈንታም እንደሚያስጨንቃችሁ የሚያጠራጥር አይደለም" በማለት የ2016 የአዲስ ዓመት መልዕክታቸውን ለአውስትራሊያ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባላት ያስተላልፋሉ።



Share