የአውስትራሊያ ፓርቲ ላይ ሊገኙ ወይም ሊያስተናግዱ አስበዋል? ሊያውቁ የሚገባዎትን እነሆን

Australia Explained - Party Etiquette

House parties are often held in the backyard when the weather allows. Credit: ibnjaafar/Getty Images

Get the SBS Audio app

Other ways to listen

አውስትራሊያውያን ዘና በሚል ባሕልና እያንዳንዷን አጋጣሚ በልዩ ኩነት ማክበር ይታወቃሉ። ይሁንና ሥነ ምግባራዊ ደንቦች በንግድ ኩነቶች ብቻ ሳይሆን፤ ደረጃውን የጠበቀም ይሁን አይሁን ሁሉም ፓርቲ ካልተደነገገ ባሕላዊ ደንቦች ጋር የተያያዘ ነው።


አንኳሮች
  • ሥነ ምግባራዊ ደንቦች ለንግድ ተቋማት ጥብቅ ናቸው፤ ማኅበራዊ መታደሞችም እምዲሁ ለጋባዥና ተጋባዥ በኩልም በተካታችንት ይጠበቃሉ
  • አውስትራሊያ ውስጥ የአንድን ሰው ቤት ሲጎበኙ አነስተኛ ስጦታ ይዞ መሔድ የተለመደ ነው፤ በተትረፈረፈ ወጪ አኳያ ሳይሆን ለጋባዥ አሳቢ መሆንን የሚያመላክት ነው
  • የልጆች ፓርቲዎች ለታዳጊ እንግዶች አነስተኛ ስጦታዎችን መስጠትን አካትቶ ከሙሉዕ ባሕላዊ ክወና ለየት ያሉ ናቸው
ለአውስትራሊያውያን የልጆች የልደት ቀናት፣ የቤት ምርቃቶችና የእራት ግብዣዎች በጣሙን አዘቦታዊ የሆኑ አከባበሮች ናቸው።

ይሁንና የቤት ውስጥ ዕድምታን ለማዘጋጀት በአብዛኛው ተገቢውን ወቅት ከመጠበቅ ያለፈ ነገርን አይሻም።

በጣሙን አስፈላጊ የሆነው የአውስትራሊያውያን በጋራ መታደም በአገሬው አዘቦታዊ የአነጋገር ፈሊጥ ‘barbie’ ተብሎ የሚጠራውና በአብዛኛው በሕዝባዊ በዓላት ወይም የሳምንቱ መጨረሻ ወቅት የሚሰናዳው የተንቀሳቃሽ ምጣድ ጥብስ ነው።
Australia Explained - Party Etiquette
When attending a business event, Ms Hardy advises against overstaying your welcome or keep partying till the early morning. Credit: xavierarnau/Getty Images
እንደ የአውስትራሊያ ሥነ ምግባር ትምህርት ቤት ዳይሬክተር ዛሪፍ ሃርዲ ኣባባል፤ በአሁኑ ወቅት የምጣድ ጥብስ ፓርቲ “አንድ ቁጥር የመዝናኛ ምርጫ ነው።" በ80ዎቹና 90ዎቹ የነበሩትን መደበኛ ሥርዓትን የተከተሉ የእራት ፓርቲዎችን ተክቷል።

አቶ ሃርዲ “የምጣድ ጥብስ በጥቅሉ ከቤት ውጪን፣ በቡድን የተሰባሰቡ ሰዎችን ያካትታል። ጥብቅ ደንብን የተከተለ ሳይሆን ዘና፤ በጣሙን ዘና ያለ ነው" ብለዋል።

ይሁን እንጂ፤ ይህ ለማናቸውም ከሥራ ጋር ተያያዥ ለሆኑ በተለይም እንደ ገና ፓርቲ ላሉ ኩነቶች የሚሆን አይደለም።
ማኅበራዊ ኩነት ሳይሆን፤ ከሥራ ተያያዥ መሆኑን ልብ ይበሉ። የሚጎነጩትን የአልኮል መጠን፤ በተለይም ተፅዕኖ የሚያሳድርብዎትን አስመልክተው ጥንቃቄ ያድርጉ። ሌላው ቀርቶ አለባበስዎ እንኳ አግባብነት ያለው መሆኑን። እናም በጣሙን አጭር የሆነ ቀሚስ ወይም በአጭር የተቆረጡ ልጥፍ ጫማዎች ወይም የተዛነፉ ሸሚዞችን መልበስ አይገባም።
ዛሪፍ ሃርዲ
አክለውም፤ በአክብሮት የተመሉ ወጎች፣ የሥራ ባልደረባዎን ወይም አለቃዎን አጉል በሆነ መልኩ መናገርን አካትቶ እስከ ኩነቱ ማክተሚያ ሙያዊ ሥነ ምግባርን የተላበሰ መሆን እንዳለበት ይናገራሉ።

የቤት ውስጥ ፓርቲዎችን በተመለከተ፤ የፈለገውን ያህል አዘቦታዊ ይሁን ሥነ ምግባር ለጋባዦችና ተጋባዦች ጠቃሚ ሆኖ ይቆያል።

“በቅድሚያ፤ አብረው መሆን የሚችሉ ዝንቅ ተጋባዥ ሰዎችን ለይተው ይወስኑ” ሲሉም አተያያቸውን ይቸራሉ።

እያንዳንዱ ተጋባዥ ምቾት እንዲሰማው መሰናዶ ማድረግ ለጋባዥ ቁልፍ ነገር ነው።

“ተጋባዦችዎ በሚደርሱበት ወቅት፤ ማዕድ ቤት ወይም ነገሮችን በማሰናዳት ወይም ጠረጴዛዎችን በማዘጋጀት እንዳይወሰኑ፤ ለእነሱ የሚሆን ጊዜ ሊመድቡ ይገባል" በማለትም አክለዋል።
ያን ለማድረግ፤ እንደሚያውቁት ማለፊያ የሞቀ አቀባበል እንዲያደርጉላቸው ፣ በወግ መሃል እንዲቀላቀሉና ሰዎችን ለማስተዋወቅ፣ መጠጥም ለመቀዳት ስንዱ መሆን ይገባል።
ዛሪፍ ሃርዲ
የቤተሰብ አካል ካልሆኑ በስተቀር ጎብኚዎች ሰው ቤት ባዶ እጃቸውን እንዲሔዱ አይመከርም።

የአውስትራሊያ ባሕር ማዶ ተማሪዎች መሥራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳም ሻርማ፤ ወደ ጋባዥ ቤት ሲሔዱ አንድ ጠርሙስ ወይን፣ ትንሽ እሽግ ምግብ ወይም ጣፋጮችን የመሰሉ አነስተኛ ስጦታ ይዞ መሔድ በትሁትነት ያስቆጥራል።

“እንዲሁም፤ ፓርቲውን ለማዘጋጀት እንዲያግዛቸው በተለይ የሚሿቸው ነገሮች ካሉ ጋባዥዎን መጠየቅ መልካም እሳቤ ነው። ስለምን፤ መስተንግዶ ማድረጋቸው በእራሱ በቂ ሥራ ነውና ጥቂት ነገሮችን ይዘውላቸው ቢሔዱ ያቃልሉላቸዋል” ሲሉም አቶ ሻርማ ያስረዳሉ።
Australia Explained - Party Etiquette
If there is leftover food that remains intact at the end of a house party, you might be offered to take some home in a container. But leave it up to the host to suggest this. Source: Moment RF / Sergey Mironov/Getty Images
አለመዘግየት የተለመደ ጨዋነት ቢሆንም ግብር ላይ ማዋልን ግድ ይላል።

አቶ ሻርማ “አውስትራሊያ ውስጥ ለፓርቲ በሰዓቱ መገኘት በጣሙን ጠቃሚ ነው። በጣሙን አይዘግዩ፤ አለበለዚያ ሁሉንም ምግብ ሊያጡ ይችላሉ! እንዲያ ሊገጥም ይችላል” ይላሉ።

ጋባዥን ጥቂት ሥራ ማገዝ አማራጭ ቢሆንም መልካም ተግባር ነው።
“ጋባዥዎን ምግብ በማብሰል፣ በማሰናዳት ሌላው ቀርቶ በማፅዳት ማገዝ ይችላሉ፤ ይህን ካደረጉ፤ ዘወትር ያስመሰግንዎታል። እንዲሁም፤ ከመሰናበትዎ በፊት ሁሌም ምስጋና ይችሯቸው።”

አቶ ሻርማ በዓለም አቀፍ ተማሪነት አውስትራሊያ የዘለቁት ከ17 ዓመት በፊት ሲሆን፤ ኢ-መደበኛ ቃላቶችን ከአውስትራሊያ አደጋገስ ጋር ከምንም ተነስተው ለምደዋል።

ጥቂት መሠረታዊ የሆኑትንም አጋርተዋል፤
  • Bubbles = ሻምፔይን 
  • BYO = የእራስዎን ይዘው ይምጡ [መጠጥ] 
  • snag = ቋሊማ 
  • bring a plate = ተጋባዦች የሚያጋሩትን ጥቂት ምግብ ይዘው እንዲመጡ መጋበዝ 
አቶ ሻርማ "የምግብ አለርጂ ካለብዎ ወይም የአመጋገብ መስፈርቶች ካለዎት፤ ቀደም ብሎ ማስታወቁ ጥሩ ልማድ ነው ወይም ፍላጎትዎን የሚያሟላ ምግብ ይዞ መሔዱ ከቶውንም የተሻለ ነው" ይላሉ።

“ግብዣን የመቀበል ማረጋገጫ መጠይቅ ላይ፤ አለርጂ ያለብዎት ወይም እንደ የእንሰሳት ምግቦችን የማይመገቡ፣ ቅጠላ ቅጠልን ተመጋቢ፣ ከግሉቲን ነፃ ምግቦችን ተመጋቢ እንደሆኑና የተወሰነ የሚጠይቁት መስፈርት እንዳለ ይጠይቅዎታል። እናም ይህንን ቀደም ብለው በማለፊያ መልኩ ያሳውቋቸው።"

“አለበለዚያ፤ እኔ እራሴ ቅጠላ ቅጠል ተመጋቢ በመሆኔ ሁሌም እንደማደርገው እነዚያን ነገሮች ይዤ እሔዳለሁ። እስካሁን በርካታ ኩነቶች ላይ ታድሜያለሁ፤ እናም አንዳንዴ ጋባዦች ለእርስዎ እኒህ ነገሮች የሌሏቸው ከሆነ መጥፎ ስሜት ይሰማቸዋል" በማለት አቶ ሻርማ ይገልጣሉ።
Australia Explained - Party Etiquette
For a birthday party held at a venue, it is customary for each guest to pay for their meal, unless otherwise offered by the host, Mr Sharma says. Credit: Thomas Barwick/Getty Images

ፓርቲዎች ለልጆች

በልጆች ፓርቲ የጋባዥ ብቸኛ ኃላፊነት የሚሆነው የምግብ መሰናዶዎችን ማመቻቸት ነው።

የሜልበርኗ የሁለት ልጆች እናት ሶኒያ ኸርዝበርግ፤ አዘቦታዊ ስለሆኑ ተጠባቂ ነገሮች ምልከታቸውን ያጋራሉ።

ወ/ሮ ኸርዝበርግ “ለልጆችና አዋቂዎች ምግብ ማቅረብ ይጠበቅብዎታል። ያለምንም ማወላወል የአመጋገብ መስፈርቶችቻውን ይጠይቁ፤ ስለምን በአሁኑ ወቅት በጣሙን ተስፋፍቷል፤ እብደት ነው። እናም፤ ሁሉንም የአመጋገብ መስፈርቶች በሚያሰኝ የምግብ ዓይነቶችን ያቀርቡና ይሰናበታሉ።"

“እንዲሁም፤ በጋባዥ በኩል እንደ ሻምፔይን የመሳሰሉ የማክበሪያ መጠጦች፣ እርጉዝ ለሆኑና የሚብላላ ጭማቂዎችንም በማቅረብ ማጉረምረም አይገባም” ይላሉ።
Australia Explained - Party Etiquette
Carers are responsible for supervising their children who are guests at a kid’s birthday party. Credit: Jason Edwards/Getty Images
በቂ ምግብ መኖሩን እርግጠኛ መሆን ጠቃሚ የመሆኑን ያህል ጋባዥ ወላጆች ለበዛ ወጪዎች ሊዳረጉም አይገባም።

ወ/ሮ ኸርዝበርግ ለልጆች ፓርቲ ተስማሚ በጀት የማይጎዳ አድርጎ ማቅረቡ የተለመደ አውስትራሊያዊ አቅርቦት እንዳለ ያመላክታሉ።

“ጣፋጭ የተነሰነሰበት ዳቦ ማቅረብ ወይም በእጅጉ አሻቅበው ምግብ አብስለው የሚያቀርቡ አብሳዮችን መቅጠር ይችላሉ። የተለያየ ነው፤ የፈለገውን ቢያቀርቡ ቅር የሚለው ሰው ገጥሞኝ አያውቅም።

“ጣፋጭ የተነሰንሰበት ዳቦ አውስትራሊያዊ ባሕል ነው። ከመቶዎች እስከ ሺህዎች አብረቅራቂ ጣፋጮችን ቅቤ በተቀባ ነጭ ዳቦ ላይ መነስነስና በአልማዝ ቅርፆች መቆራረጥ ነው። አለያም፤ የፓርቲ ፓይ በጣሙን አውስትራሊያዊ ባሕል ነው” ብለዋል።

ለጋባዥ ወላጆች ተጋባዥ ልጆች ወደ ቤታቸው ይዘዋቸው የሚሔዱ አነስተኛ ስጦታዎችን ‘የፓርቲ ከረጢቶች’ ውስጥ አድርጎ ማዘጋጀት የተለመደ ነው።
Australia Explained - Party Etiquette
Ms Hardy from the Australian School of Etiquette advises against bringing expensive gifts at a kids’ party. “You do not need to be showing status or proving anything by buying ridiculously priced gifts.” Credit: Nick Bowers/Getty Images
ለአነስተኛ ፓርቲ ተስማሚ ከሆነ መታሰቢያነት ያለፈ ውድ እንዲሆን አይጠበቅም።

ወ/ሮ ኸርዝበርግ ለአምስት ዓመት ወንድ ልጃቸው ልደት ስላዘጋጁት ሲያስረዱ፤

“ትንሽዬ አጉሊ መነፅር፣ በቀለም የተሸለመ እርሳስና እራሳቸው የሚፅፉበት ባዶ ካርድና መልኮችን የሚሠሩበት አነስተኛ ማጣበቂያዎችን ገዛን" ብለዋል።
እናም፤ ፓርቲውን የሚያስታውሱበትና ወደ ቤታቸው ይዘውት የሚሔዱት ትንሽዬ ቅርፃ ቅርፅ መሰል ነገር ነው። እርግጥ ነው፤ የሶስት ዓመት ዕድሜን ሲያልፉ ሁሌም ትንሽ ጣፋጭ ውስጡ ይኖራል።
ሶንያ ኸርዝበርግ
በተመሳሳይ መልኩ፤ የልደት ስጦታ ዋጋው ሳይሆን ዕሳቤው ነው የሚቆጠረው ሲሉ ልብ ያሰኛሉ።

“ልደታቸውን ለሚያከብሩ ልጆች፤ ምን እንዳገኙ ሳይሆን፤ እውነታው ልደታቸውን ከሚወዷቸው ጓደኞቻቸው ጋር ሆነው መደሰትን ነው። ስጦታዎችን ማግኘታቸው ትልቅ ነገር ነው፤ ይሁንና ስጦታው ምን እንደሆነ አያስታውሱትም። የሚያስታውሱት ምንድነው፤ ያሳለፉትን ጊዜ ነው" ሲሉ ያጠቃልላሉ።

Share