የአውስትራሊያን የውርስ ሕጎች መፍታት፤ የእርስዎ መብቶችና ግዴታዎች ሲብራሩ

Australia Explained - Inheritance Laws

Who inherits if there is no Will? Credit: AlexanderFord/Getty Images

ምንም እንኳ ጥብቅ የውርስ ሕጎች ተደንግገው ያሉ ቢሆንም፤ አውስትራሊያውያን የንብረቶች ውርስ ግብር አይከፍሉም። ከ50 ፐርሰንት በላይ አውስትራሊያውያን ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ የኑዛዜ ውል ሳያሰፍሩ በመሆኑ ፍርድ ቤት አዘውትሮ ጣልቃ ይገባል።


አንኳሮች
  • አውስትራሊያውያን የውርስ ግብር አይከፍሉም።
  • ውርስን ለመከወን አስፈፃሚ አስተዳደር ይመደባል።
  • ውርስ ቀላል የሚሆነው የኑዛዜ ውል ሲኖር ነው፤ አለያ ግና ፍርድ ቤቶች ጣልቃ ሊገቡ ይችላሉ።
ሰዎች ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ፤ ትተዋችው የሚያልፏቸው ነገሮች ሁሉ 'የሟች ንብረት' ይሆናሉ። ንብረቶቻቸውም ለቤተሰብ፣ ጓደኛች ወይም ድርጅቶች ሊተላለፉ ይችላሉ።

“ንብረቶች ሲባሉ ቤቶችና የባንክ ተቀማጭ ገንዘብ፣ መኪናዎች፣ አክሲዮኖች ወይም የቤት ውስጥ ቁሳቁሶችን የመሳሰሉ የንግድ ዋጋ ያላቸው ሊሆኑ ይችላሉ። እንዲሁም፤ ጌጣ ጌጦችን የመሳሰሉ ስሜታዊ ቁርኝት ያላቸው ቁሶችም ይሆናሉ"

“አንድ ንብረት በስጦታ በተለይ ሊሰጥ ይችላል፤ መኪናዬን ለእንቶኔ ወይም ለጎረቤቴ እንቶኒት $10,000 ሰጥቻለሁ፤ ወይም ለምሳሌ ጠቅላላ ንብረቴን ለልጆቼ አውርሻለሁ በማለት ንብረት ሊተላለፍ ይችላል” ሲሉ የቪክቶሪያ ክፍለ አገር ባለ አደራ አገልግሎቶች የሥራ አስፈፃሚ ዋና አስኪያጅ ሜሊሳ ሬይኖልድስ ያስረዳሉ።

ውርስ አስፈፃሚ ምንድነው?

የኑዛዜ ውል አንድ ግለሰብ በሞት ከተለየ በኋላ የውርስ ፍላጎቶቹ እንደምን በውርስ መከፋፈል እንዳለባቸው ቃል የሠፈረበት ሰነድ ነው።

በኑዛዜ ውል ላይ፤ በንብረት ባለ አደራ ሕጋዊ አካል ያለው ውርስ አስፈፃሚ በመባል ይታወቃል። የውርስ አስፈፃሚ ኃላፊነት የሟች ፍላጎቶች ግብር ላይ መዋላቸውንና ግዴታዎችም መፈፀማቸውን ማረጋገጥ ነው።

ውርስ አስፈፃሚ እራሱ ባለ ድርሻም ሊሆን ይችላል።

ፊሊፒንስና አውስትራሊያ በሕግ ባለ ሙያነት የሠሩና እየሠሩ ያሉት ፍሎራንቴ አባድ፤ ውርስ አስፈፃሚ ያልተመደበ እንደሁ ፍርድ ቤቶች ጣልቃ እንደሚገቡ ሲገልጡ፤
“አመልካች ባለ አደራ ወይም አስተዳዳሪ ተብሎ ይጠራል"

“እናም በኑዛዜ ውል ላይ ውክልና የተቸረው ውርስ አስፈፃሚ ሲሆን አስተዳዳሪ በፍርድ ቤት የተመደበ ባለ አደራ ነው” ሲሉ ያስረዳሉ።

ውርስ አስፈፃሚ ሆነው የተወከሉና ግና ኃላፊነትዎን መወጣት የማይችሉ ሆኖ ከተሰማዎት፤ የመንግሥት ባለ አደራዎች እርስዎን እንዲወክሉ ውክልና መስጠት ይችላሉ። ተወካይ የሚሆነውም የመንግሥት ኤጀንሲ የሕይወት ፍፃሜ ጉዳዮችን ከዋኝ ድርጅት ነው።

ውርስ አስፈፃሚ ወይም አስተዳዳሪ ወራሾችን ማሳወቅና ለጠቅላይ ፍርድ ቤት የውርስ ማዘዣ የማመልከት ግዴታ አለበት።
Australia Explained - Inheritance Laws - Supreme Court
Melbourne Supreme Court issued widespread Australian gagging order over political bribery allegations revealed by 'Wikileaks' today 30-July-2014 Melbourne Australia Credit: Nigel Killeen/Getty Images

የፍርድ ቤት ውርስ ማዘዣ ምንድን ነው?

የፍርድ ቤት ውርስ ማዘዣ የኑዛዜ ውሉን ሕጋዊነት የሚያላብስና ውርስ አስፈፃሚ የንብረት ውርስ አፈፃፀም ተግባሩን እንዲከውን ፈቃድ የሚቸር ነው።

ጠቅላይ ፍርድ ቤት የውርስ ማዘዣ ማመልከቻ ሬኮርዶችን መዝግቦ ያስቀምጣል። የአካባቢዎን የጠቅላይ ፍርድ ቤት የውርስ ማዘዣ ምዝገባ መመልከት ይችላሉ።

ኑዛዜ ከሌለ ወራሽ ማን ይሆናል?

“አንድ ግለሰብ የኑዛዜ ውል ሳይተው ሕይወቱ ሲያልፍ 'ያለ ኑዛዜ ውል ሕይወቱ ያለፈ ሰው ንብረት' ተብሎ እንደሚጠራ ሜሊሳ ሬይኖልድ ያመላክታሉ።
በእያንዳንዱ ክፍለ አገር በተለይ ማንና በምን ያህል ፐርሰንት ንብረት እንደሚወርስ የተዘረጋ የቀመር ድንጋጌ አለ።
ሜሊሳ ሬይኖልድስ
“ለንብረት ወራሽነት የላቀ መብት አለው ተብሎ የሚታሰብ ግለሰብ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት የውርስ ማዘዣ ለማውጣት ማመልከት ይችላል ወይም ለአንድ የሕዝብ ባለ አደራ የንብረት አስተዳዳሪነት ውክልና መስጠት ይችላል” ሲሉም ሬይኖልድስ ይናገራሉ።

ንብረቶችን ያለ ኑዛዜ ውል የሚያከፋፍለው ቀመር አጠቃቀም የመተካካት አንቀጽ ተብሎ ይጠራል።

ምንም እንኳ የእያንዳንዱ አካባቢ አተገባበር የተለያየ ቢሆንም፤ አብላጫ ንብረቶች ለሟች ባለቤት ሲተላለፍ የተቀረው የልጆች ድርሻ ይሆናል።

ልጆች ሳይኖሩ ባለቤት ወይም ሕጋዊ ጋብቻ አልባ አብሮ ኗሪ የፍቅር ጓደኛ ሲኖር፤ ንብረቱ ለሟች ባለቤት ወይም ሕጋዊ ጋብቻ አልባ አብሮ ኗሪ የፍቅር ጓደኛ ይተላልፋል። ባለቤት ወይም ሕጋዊ ጋብቻ አልባ አብሮ ኗሪ የፍቅር ጓደኛ ወይም ልጆች ከሌሉ በተጠቃሽ ድንጋጌ ንብረት በቀጣይነት ቅርብ ለሆነ ዘመድ የሚተላለፍ ይሆናል።

ለውርስ የሚበቃ ማንም ሰው ከሌለ የንብረቱ ተረካቢ መንግሥት ይሆናል።
Australia Explained - Inheritance Laws
Cropped shot of a senior couple meeting with a consultant to discuss paperwork at home Credit: shapecharge/Getty Images

የግብር ግዴታዎቼ ምንድን ናቸው?

አውስትራሊያውያን የውርስ ግብር የማይከፍሉ ቢሆንም፤ ሌሎች የፋይናንስ ግዴታዎች ግና አሉ።

የወረሱትን ንብረት የሚሸጡ ክሆነ የአውስትራሊያ ግብር ቢሮ የግብር ደንቦችን ያስፈጽማል።

ባለ ሕጋዊ ፈቃድ የሂሳብ ባለሙያው አክራም ኤል-ፋህክሪ ይህን ሲያስረዱ “የሟች መኖሪያ ቤት ከሆነ የሟች ንብረትን አስመልክቶ ተከታይ መዘዞች አይኖሩም" ይላሉ።

በውርስ የተገኘው መኖሪያ ቤት በሁለት ዓመታት ውስጥ ከተሸጠ ከካፒታል ትርፍ ግብር ነፃ ይሆናል። እናም የባለ ሙያ ምክርን መጠየቅ የተሻለ ይሆናል።

ወደ ጥሬ ገንዘብነት የተለወጡ አክሲኖች የካፒታል ትርፍ ግብርን ያስከትላሉ፤ እንዲሁም ከጥሬ ብር የተገኘ የባንክ ወለድ ካለ ግብርዎን ሲያሠሩ በገቢነት የማሳወቅ ግዴታ ይኖርብዎታል።

የባሕር ማዶ ንብረት ውርስ

የሁለት ዓመታቱ ክፍተት በባሕር ማዶ የውርስ ንብረት ላይም ተፈፃሚነት እንደሚኖረው አክራም ኤል-ፋህክሪ ሲያመላክቱ፤

“ንብረቱ አውራሽ በሞተ ሁለት ዓመታት ውስጥ ተሸጦ ገንዘቡ ወደ አውስትራሊያ ከመጣና ከተገለጠ፤ በአውስትራሊያ ደንቦች መሠረት ከግብር ነፃ ይሆናል”

“አንድ ሊኖር የሚችል ችግር ቢኖር ንብረቱ የተሸጠበት አገር የተለየ የግብር ሕጎች ካሉት ነው። ያኔ የገንዘብ ዝውውሩ በእዚያ አገር የግብር አሠራር መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል” ይላሉ።

የአውስትራሊያ ነዋሪ ካልሆኑ ልዩ የካፒታል ትርፍ ግብር ተፈፃሚነት ሊኖረው ይችላልና የባለ ሙያ ምክርን መጠየቅ ተመራጭ ይሆናል።
Australia Explained - Inheritance Laws
codicil to a last will and testament and irrevocable trust being signed by a 50 year old woman. Credit: JodiJacobson/Getty Images

ውርስን መቀናቀን እችላለሁ?

ውርስ የሚገባዎት እንደሆነ የሚያምኑና ሆኖም በኑዛዜ ውል ውስጥ ያልተካተቱ ከሆነ፤ ወይም የኑዛዜ ውል ከሌለ በተተኪ አንቀፅ መሠረት የመቀናቀን መብት ይኖርዎታል። ይህም የቤተሰብ ጥያቄ አቅርቦት ይባላል።

ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኑዛዜውን ማስተካከል ይችላል።

ይሁንና፤ ማንም ሰው ወዲያውኑ የውርስ መብት እንደማያገኝና የይገባኛል አቅርቦት ጥያቄዎን ሊያረጋግጡ እንደሚገባ ያሳስባሉ።
ያለዎትን ገንዘብ ነክ ግንኙነትና እንደምን ሟች በማለፉ ሳቢያ እንደታገዱ፤ በኑዛዜውም መሠረት በቂ የሆነ ሰነድ ያልቀረበልዎ ስለ መሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ ይጠበቅብዎታል። አዋኪ ወይም ፈጣን የሆነ ውሳኔ አይኖርም፤ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከእርስዎ የጥያቄ አቅርቦት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ አስገብቶ የሚመለከተው ይሆናል።
ፍሎራንቴ አባድ
ውርስ ሊወሳሰብ ይችላል፤ ይሁንና እንደ እና ን በመሳሰሉ ድርጅቶች አማካይነት እገዛዎች ይኖራሉ። በአካባቢዎ ያሉ ቋንቋዎን የሚናገሩ ጠበቆችን ወይም የሟች ንብረት ጥብቅናን የሚሠሩ የሕግ አገልግሎት ሰጪዎችን ዝርዝር ይሰጥዎታል።

እንዲሁም፤ ስለ ኑዛዜ ውል አሠፋፈርና ለመንግሥት ባለ አደራዎች የሚያገለግል ውርስ አስፈፃሚን እርስዎ ባሉበት ክፍለ አገር ወይም ክፍለ ግዛት እንደምን ነፃ መመሪያዎችን ማግኘት እንደሚችሉ ተደራሽ የሆኑ ድረ ገፆች አሉ።

Share