የማይፈለጉ ልብሶችን መክላት

Australia Explained: Clothing Waste - Woman folding laundry

It can be fun to clean out your wardrobe while addressing excessive consumption. Credit: Cavan Images/Getty Images

Get the SBS Audio app

Other ways to listen

አውስትራሊያውያን በየዓመቱ ከ 200,000 ቶኖች በላይ ልብሶችን የቆሻሻ መጣያ ውስጥ ይጥላሉ። ያም 10 ኪሎ ግራም በነፍስ ወከፍ ማለት ነው። የአውስትራሊያን ጨርቃ ጨርቅ ብክነት ቀውስ መልሶ ጥቅም ላይ እንዲውል በማድረግ፣ በችሮታና የማያስፈልጉንን ልብሶች በመለዋወጥ መታደግ እንችላለን።


አንኳሮች
  • ልብሶችን በጭራሽ የቤተሰብዎ መልሶ ጥቅም ላይ የማዋያ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ውስጥ አያኑሩ
  • የተወሰኑ ትላልቅ ቸርቻሪዎች መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል በማናቸውም ሁኔታ ያሉ ልብሶችን ይቀበላሉ
  • ጥሩ ይዘት የሌላቸው አልባሳት በአካባቢ ተፈጥሮና በጎ አድራጎት ድርጅት ወጪ ለቆሻሻ መጣያ ይዳረጋሉ
የአውስትራሊያ ፋሽን ምክር ቤት በየዓመቱ በአማካይ 56 አዳዲስ ልብሶችን እንደምንገዛ በሪፖርቱ ገልጧል።

በተለይም የ አልባሳቶቻችን ፈጥነው ይወይባሉ፣ ይበላሻሉ ወይም አሰልቺ ይሆናሉ፤ እናም ኃላፊነት በተመላበት ሁኔታ ልንከላቸው ይገባል። ያም ማለት ለቆሻሻ መጣያ ሳንዳርጋቸው ለችሮታ ወይም መልሰው ለጥቅም እንዲውሉ በማድረግ።

የእርስዎ መልሶ ጥቅም ላይ የማዋያ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ መልስ አይደለም

“ወርቃማው ደንብ ልብሶች፣ ጫማዎች፣ ጨርቅ፣ አንሶላዎች ወይም ፎጣዎች ወይም ማናቸውም ዓይነት ጨርቃ ጨርቆችን ከጎዳና ጥግ ካለ መልሶ ጥቅም ላይ የማዋያ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ውስጥ መክተት አይደለም" ሲሉ የኧርክ ፕላኔት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ረቤካ ጊሊንግ ያስረዳሉ።
የጨርቃ ጨርቆች ወደ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ የመግባት ችግሩ፤ ተመልሰው ጥቅም ላይ ካለመዋላቸው ሌላ፤ ወደ መልሶ ጥቅም ላይ የማዋያ ማሽን ውስጥ ሲገቡ ሁሉም ነገር አልፈጭ ብሎ እንዲገታ ያደጋሉ።
ረቤካ ጊሊንግ፤ የኧርክ ፕላኔት ዋና ሥራ አስፈፃሚ
አገልግሎት ሰጪው የእርስዎን ተፈላጊ ያልሆኑ አልባሳት ወስዶ በማሰናዳት ተፈጭተው ለአገልግሎት እንዲበቁ ወይም ጥቅም ላይ እንዲውሉ ያደርጋል።
Australia Explained: Clothing Waste - donation bin
Source: Moment RF / Andrew Merry/Getty Images

ልብሶችዎን ለ 'ዕድል ሱቅ' ይለግሱ

አውስትራሊያውያን የማይፈለጉ ልብሶችን ለግብረ ሰናይ ድርጅት መለገስን ይወዳሉ። 'ዕድል ሱቅ' በመባል ለሚታወቀው የግብረ ሰናይ ድርጅቶች ሱቅ ወይም በአካባቢዎ ካሉ ሱቆች አቅራቢያ ከሚገኝ ማጠራቀሚያ ልብስዎችዎን ወስዶ መቸር የሚያስከትልብዎ ወጪ የለም።

የዕድል ሱቆች የችሮታ አልባሳትን በመላ አውስትራሊያ ለችግረኞች በመሸጥ አንድ ቢሊየን ዶላር ያህል ያገኛሉ።

ይሁንና፤ ምንም እንኳ ዕሳቤዎቻችን ማለፊያም ቢሆኑ ልገሳዎቻችን ላይ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል።

ወ/ሮ ጊሊንግ ይህንኑ ሲያስረዱ “ሰዎች ተለባሽ የማይሆኑ ወይም በእጅጉ ያለቁ ወይም ጊዜ ያለፈባቸውን አምጥተው እንዲያስቀምጡ አንሻም። ስለምን፤ በረድኤት ድርጅቶች ወጪ ወደ ቆሻሻ ተወስደው ያጣላሉና”

“የችሮታ ሱቆች በአሁኑ ወቅት በዓመት $13 ሚሊየን ዶላር ያህል የማይፈለጉ ልብሶችና ቁሳ ቁሶች በማጠራቀሚያዎቻቸው ውስጥ ይቀመጡላቸዋል” ይላሉ።

እንደ ኦሜር ሶከር፤ የመልሶ ጥቅም ላያ ማዋል ረድኤት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አባባል፤ ቀላል የችሮታ ጥራት መለኪያ መንገድ አለ።
ለጓደኛዎ መስጠት የማይሹትን፤ እባክዎን ለችሮታ አይለግሱ።
እንደ ኦሜር ሶከር፤ የመልሶ ጥቅም ላያ ማዋል ረድኤት አውስትራሊያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ
አክሎ በመላ አውስትራሊያ ያሉ የዕድል ሱቆችን ዝርዝር ፈልገው ማግኘት ይችላሉ።
  • Vinnies
  • Australian Red Cross
  • Save the Children
  • Lifeline
  • Anglicare
  • Brotherhood of St Laurence
ድረ ገፁ በእያንዳንዱ ልገሳዎ የካርቦን ብክለትን አስልቶ የሚያሳይ የ ‘መልሶ መጠቀም ተፅዕኖ’ መለኪያ ቁስ አለው።
Australia Explained: Clothing Waste - Ol wokman oli sortem aot ol klos
Workers sorting out clothing at the St Vincent de Paul Society, a major charity recycling clothes, in Sydney. Source: AFP / PETER PARKS/AFP via Getty Images

አልባሳትዎችዎን መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል ያበርክቱ

ልብስዎችዎ የ 'ጓደኛ መመዘኛ' ን ካላለፈ መልሶ ጥቅም ላይ የማዋል የተወሰኑት ዋነኛ ቸርቻሪዎችን ፕሮግራምን ይመልከቱ።

“ኤች እና ኤም በተመረጡ ሱቆች በማንኛውም ሁኔታ ላይ ያሉ ማናቸውንም ዓይነት ልብሶችና ጨርቃ ጨርቆች በነፃ ተቀብሎ መልሶ ጥቅም ላይ የማዋል ፕሮግራም አለው”

“በተመሳሳይ መልኩ፤ ዛራ በተመረጡ ሱቆቹ እንዲሁ ነፃ የጨርቃ ጨርቅ ስብሰባ ፕሮግራም አለው። ዩኒግሎ የራሳቸው የሆነ መለያ ያላቸውን ሆነው በማንኛውም ዓይነት ሁኔታ የሚገኙ ልብሶችን በነፃ መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል ፕሮግራም ይቀበላሉ። እንዲሁም፤ ፓታጎኒያ በደንበኞቹ ተለብሰው ያረጁ ወይም የተበላሹ በዕውቅ የተሠሩ ውድ ልብሶቹን የሱቅ ነጥቦችን በመስጠት ይቀበላል” ሲሉ ወ/ሮ ረቤካ ጊሊንግ ይገልጣሉ።

ተሳታፊ ሱቆችን ፈልገው ለማግኘት ድረ ገፅን ይጎብኙ።

የአካባቢዎ ማዘጋጃ ቤት ምናልባትም እንዲሁ የልብስ ችሮታ ማጠራቀሚያ ይኖረው ይሆናል።

ፕላኔት ምድር ኒው ሳውዝ ዌይልስ፣ ቪክቶሪያና ኩዊንስላንድ ውስጥ የስፖርት ጫማ ችሮታዎችን ይቀበላል። አትራፊ ያልሆነ ድርጅት ሲሆን፤ በጥሩ ሁኔታ ላይ ያሉ የመሮጫ ጫማዎችን ዳግም ጥቅም ላይ እንዲውሉ በመላው ዓለም ችግረኛ ለሆኑቱ ይለግሳል።

የልብስ ልውውጥ ኩነት ላይ ይገኙ

በአልባሳት ልውውጥ እንደሚካሔደው ዓይነት የልብስ ልውውጥ ኩነቶች የሞቀ ተቀባይነት እያገኙ ነው።

“እዚህ ሲድኒ ውስጥ ከአልባሳት ልውውጥ ጋር እያደረግን ያለነው የልብስ ልውውጥ ልባሳቸው ከቶውንም ለጠበባቸው ወይም ለሰለቻቸው ሰዎች ማለፊያ አጋጣሚ ነው” ሲሉ የሲድኒ ከተማ ከንቲባ አዳም ዎርሊንግ ያስረዳሉ።

ከቅጥ ያለፈ ፍጆታን እያመላከቱ የልብስ ቁም ሳጥንን ማፅዳት አንድ መደሰቻ ነው።

“የምናደርገው ምንድነው አልባሳትን ከቆሻሻ አውጥተን ለአንድ ሰው በአንድ ወቅት እርስዎ ወድደውት የነበረውን እንዲወደው ዕድል መስጠት ነው” ሲሉ ዎርሊንግ ይናገራሉ።

በመላ አውስትራሊያ በቅርቡ ስለሚካሔዱት የልብስ ልውውጥ ኩነቶች ድረ ገጽን ይጎብኙ።
Australia Explained : Clothing Waste - ol klos long
Ol hangem ol klos long hanga. i gat ol diferen kaen klos mo hanga long wan klos exchange parti. Source: Moment RF / Marissa Powell/Getty Images

'የዝውውሮሽ ምጣኔ ሃብት'ን ይደግፉ

የአልባሳታችንን ጠቅላላ የዕድሜ ዘመን ከግምት ውስጥ ማስገባት ያሻናል። ችሮታን መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል አውስትራሊያ ሁላችንም በቻልነው መጠን የሸመታ ፍጆታን ቀንሰን ድጋሚ መጠቀምን ወይም የመልሶ ጥቅም ላይ የማዋል 'የዝውውሮሽ ምጣኔ ሃብት' ትልማችን ሻምፒዮና ነው።
እንደ እውነቱ የምርቶች መልካም ተከባካቢ ስለ መሆን ነው
ኦሜር ሶከር፤ የመልሶ ጥቅም ላያ ማዋል ረድኤት ዋና ሥራ አስፈፃሚ
“ያ ለአልባሳት ምን ማለት ነው፤ ከምር የሚያስፈልግዎትን ዓይነቶች ይግዙ፣ ለረጅም ጊዜያት እንዲቆዩ ያድርጓቸው፣ ይጠግኗቸው፣ የመከያቸው ጊዜ ሲደርስም በጥሩ ሁኔታ ላይ ያሉ ከሆነ ለረድዔት ድርጅት ይችሯቸውና እነሱ ሌላ ቤት ይፈልጉላቸው”

“ወይም በመጥፎ ሁኔታ ላይ ያሉ ከሆነ ወይም ሊከሉ ግድ የሚሰኙ ከሆነ ተገቢ የሆነ መንገድ ይፈልጉላቸው” በማለት አቶ ሶከር አቅጣጫ ያመላክታሉ።

Share