አውስትራሊያ ውስጥ ወዳጆችን ያፍሩ፤ የባሕል ተሻጋሪ ወዳጆች ጠቀሜታ

Settlement Guide: Cross cultural friendships

International students report better experiences when they make local friends. Source: iStockphoto / Dedy Andrianto/Getty Images

Get the SBS Audio app

Other ways to listen

አዲስ አገር ውስጥ ሰዎችን ከሚገጥሟቸው ብርቱ ተግዳሮቶች አንዱ ጓደኞችን ማፍራት ነው። ከእኛ ጋር ባሕላዊ ተመሳሳይነትነት ካላቸው ጋር በቀላሉ የድጋፍ አውታረ መረቦችን እንመሠርታለን፤ ይሁንና የጓደኝነት መረብን ከሌሎች ጋር አስፍቶ መዘርጋትን አማትረው ያስቡ። ባሕል ተሻጋሪ ወዳጅነቶች አተያዮን ያዳብርልዎታል፤ ሲልም የእርስዎን ከሌሎች ጋር የተዋሃጅነት መንፈስ ከፍ ያደርጋል።


አንኳሮች
  • በባሕል ተሻጋሪ ወዳጅነቶች ውስጥ በተለያየ የፍልሰት ተሞክሮዎች ውስጥ ተመሳሳይነትን ፈልገን እናገኛለን
  • ባሕላዊ ግርዶሽ በአዲስ አገር ሁነኛ መረጃን ከማግኘት ይገታናል
  • ባሕላዊ ተሻጋሪ ወዳጅነቶች የተለየ አመለካከትን ያጎናፅፉናል፤ የተዋሃጅነት መንፈሳችንንም ያጠነክሩልናል
  • እራሳችንን በአንድ ባሕላዊ ክቦሽ መወሰን በጣሙን ትርጉም ያላቸውን ወዳጅነቶች የመፍጠር ቅማችንን ይነሳናል
ጓደኞችዎ ከእርስዎ ባሕላዊ ክብ ውስጥ ናቸው?

የፍልሰት ተሞክሮ ብቸኛ ሊያደርግ ይችላል፤ መረዳት በሚያስችል መልኩ ለእርዳታና ወዳጅነት ከእኛ ጋር ተመሳሳይ ወደ ሆኑ ሰዎች እንሳባለን።

ይሁንና ከእራሳችን ባሕላዊ ክብ ወጣ ማለቱ ለተለየ አተያይ ይጋብዘናል፤ የርህራሔ መንፈሳችንንም ይበልጥ ያንፅልናል።

ባሕል ተሻጋሪ ወዳጅነት የጋራ ተመሳሳይነታችንን ያንፀባርቃል።

የወዳጅነትና ፍልሰት ተጠባቢዋ ዶ/ር ሃሪየት ዌስትኮት “ሰዎች ወደ አውስትራሊያ ሲመጡ በአብዛኛው በፍልሰት ተሞክሮዎቻቸው ይወዳጃሉ"

“የተለያዩ የፍልሰት ዓይነቶች አሉና ሰዎች የሚፈልሱባቸው ምክንያቶች የተለያዩ ናቸው። ያለፉባቸው የፍልሰት መንገዶችም እንዲሁ ሊለያዩ ይችላሉ። ሰዎችን ስለ ተሞክሯቸው መጠየቁ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፤ እንዲሁም መንፈስን አዋኪ ሊሆንም ይችላልና በወዳጅነት ወቅት ጥንቃቄ ሊያደርጉበት ከሚገቡ ጉዳዮች አንዱ ነው" ይላሉ።

ባሕላዊ 'ግርዶሽ’

እንደ እኛው ከሚያስቡ የእራሳችን አገር ዜጋ፣ ባሕላዊ ወይም የጎሳ ክቦሽ ውስጥ ምቾት ሊሰማን ይችላል፤ ይሁንና ውስንነትም ይኖራል።

“እናም፤ ችግሩ ተከልለው ካሉበት ከእዚህ ግርዶሽ ተሻግረው አያልፉም” ሲሉ በሮያል ሜልበርን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የዝንቅ ማኅበረሰባት ተግባቦት ተጠባቢ የሆኑት ፕሮፌሰር ካትሪን ጎሜዝ ይናገራሉ።
በግርዶሽ ውስጥ ሲሆኑ የሚያስቡት እኔ በማስብበት መንገድ ነው። እናም በምኖርበት መዳረሻ አገር የሚኖረኝ መረጃና አተያይ ጓደኛዬ ያለው ዓይነት ነው። ያም አዋኪ ይሆናል፤ ስለምን እንደ እውነቱ ከሆነ ስለሚኖሩበት የውጭ አገር ግንዛቤ የለዎትምና።
ካትሪን ጎሜዝ
ከእዚያ ግርዶሽ ባሻገር መረጃን ማግኘት በመዳረሻ አገራችን ለመኖር በእጅጉ አስፈላጊ ነው።

ዓለም አቀፍ ተማሪዎች በባሕል ግጭት መታወክን አስመልክቶ ሪፖርት የሚያደርጉት በጥቂቱ ነው። ከአገሬው ሰዎች ጓደኞችን ሲያፈሩ በተሻለ ሁኔታ እራሳቸውን ያዋህዳሉ።

ይሁንና ፕሮፌሰር ጎሜዝ በርካታ ቻይናውያን ዓለም አቀፍ ተማሪዎች ከቻይናውያን ክብ ውጪ ጓደኞች እንደሌላቸው ሰምተዋል።
pexels-kindel-media-7149165.jpg
Make friends in Australia: the importance of cross-cultural friendships
“ሁሉም ‘አዎን፤ በዓለም አቀፍ ተማሪነት ተሞክሯችን በጣሙን ደስተኞች ነን፤ ይሁንና ትልቁ ፀፀታችን ከአገሬው ሰዎች መካከል ጓደኞችን አለማፍራታችን ነው’ ይላሉ።

“ሆኖም ፍትሐዊ ለመሆን፤ ስለ እውነት ለአያሌ ጊዜያዊ ፍልሰተኞች ከአገሬው ሰዎች መካከል ጓደኞችን ማፍራት አስቸጋሪ ነው” ብለዋል።

ጓደኞችን ማፍራት አዋኪ ነው

የአገሬው ሰዎች በእዚያ የቆይታ ዓመታቸው ውስጥ ጓደኞችን ያፈሩና ወደ ባሕላዊ ክባቸው ይነጉዳሉ።

የቀድሞው የሩስያ ዓለም አቀፍ ተማሪ ማክስ ቲካቼንኮ ይህንን መራር እውነታ እዚህ እንዳረፈ ተገንዝቦታል።
የተወሰኑ ፍልሰተኞች እኒያን ማኅበራዊ ክቦሽ ጥሶ ለመዝለቅ አዋኪ ነው ማለታቸው ሲሰማ፤ እኒያን ተግዳሮች እረዳለሁ። በእዚያ ውስጥ አልፌያለሁና።
ማክስ ቲካቼንኮ
አቶ ቲቼንኮ “ይሁንና የግለሰብ እራስን የማግለል ገደቦች አስመልክቶ ለመናገር ድክመት የተመላበት ሰበብ ነው ለማለት ግድ እሰኛለሁ” ብሏል።

ዶ/ር ዌስትኮት ጓደኝነት በፈቃደኝነት የሚሆን ነውና ሁሉም ሰው ጓደኛችን ሊሆን እንደማይሻ ሲናገሩ፤

“እኛ በመሆናችን ሳይሆን፤ እውነታው የእነሱ ሕይወት በውጥረት የተመላ ከመሆን አኳያ ነው። አዕምሯችንን ክፍት አድርገን እንደ ጉዞ ከወሰድነው፤ በሂደት ፈቃደኛ የሚሆኑ ይገጥሙናል” ብለዋል።

ባሕላዊ ክቦሾችን ጥሰው ይውጡ

ማክስ ቲቼንኮን ከባሕላዊ ክቡ ወጥቶ እንዲቃኝ ግድ ያሉት የማወቅ ጉጉትና ትርጉም ያለው ወዳጅነት ፍለጋ ናቸው።

“ልክ ሕፃን ልጆችን የከረሜላ ሱቅ ውስጥ የማየት ያህል አድርጌ ነው የማስበው”

“ሁሉንም መሞከር ይሻሉ። አውስትራሊያን በተመለከተ ባሕላዊ የከረሜላ ሱቅ ጎዳና ላይ ማግኘት ትችላላችሁና፤ እራስን መገደቡ የሚያሻው ለምንድን ነው?” ሲል ተናግሯል።
Settlement Guide: Cross cultural friendships
People born and raised in Australia can exist in a cultural bubble too. Credit: SolStock/Getty Images
ምክሩ ቀላል ነው፤ ይውጡና ይሞክሩ ነው።

“እራስዎን በእራስዎ ባሕል ውስጥ ገድበው ካስቀሩ ሊያዳብሩ ይችሉ የነበረውን በጣሙን ትርጉም ያለው ጓደኝነት ሊያገልሉ ይችላሉ” ማለት ነው ባይ ነው።

ተስማሚነት

ሲንጋፖር የተወለዱት ፕሮፌሰር ጎሜዝ ማንነት በአውሮፓዊት-እስያዊትነት ይገለጣል። አውስትራሊያ እንደዘለቁ ከእሳቸው ለየት ካሉት ጋር ሁሉ ይነጋገሩ ነበር።

አሁን አካል የሆኑበትን ሰፊውን ማኅበረሰብ መረዳት ማለት ነው፤ እንዲሁም ዙሪያ ገባውንም ማወቅ እንደሚገባዎት ሲያመላክቱ፤

“ለምሳሌ ያህል አውስትራሊያውያን ጓደኞች ያለዎት ከሆነ፤ ያ ዓይነቱ የስሙምነት መንፈስ በጣሙን ትልቅ ነው።
በትክክል እራስዎን ከመሰሉ ሰዎች ጋር ጊዜዎን የሚያሳልፉ ከሆነ፤ እራስዎን ካሉበት ሥፍራ ተሞክሮዎች ጋር አላስማሙም። ከአገርዎ ዙሪያ ገባው በትንሹ ለየት ያለ አገር ነው ያሉት ማለት ነው። እንዲያ ነው።
ማክስ ቲካቼንኮ
Settlement Guide: Cross cultural friendships
Being friendly and giving people the benefit of the doubt can go a long way to forming friendships. Credit: Lucy Lambriex/Getty Images
የእራስን ባሕላዊ ክቦሽ ጥሶ ስለመውጣት ሲነሳ፤ ሰዎች ስለ ፍርሃትና አዋኪነቱ እንደሚናገሩ አቶ ቲቼንኮ ይገልጣል።

“ሊፈሩ የሚገቧቸው፤ በሌላኛው ፍርሃት የሚያጧቸውን ነገሮች ነው”

“ፍርሃትን ይግፉና ወደ አስደሳቹ ነገር ይዝለቁ። ወጣ ብለው ቀልድ ጣል ሊያደርጉ፣ ዝምታን ሊሰብሩና እምብዛም ሳይቆዩ ግለሰቡ እውስትራሊያ የተወለደ ይሁን ወደ አውስትራሊያ የመጣ ያ ምንም ማለት አይሆንም" ብሏል።

Share