ተዋናይት ሰናይት መብራህቱ፤ ከአገር ቤት እስከ አውስትራሊያ

Community

Actress Senayt Mebrahtu. Source: Pablo Lanta/S. Mebrahtu

Get the SBS Audio app

Other ways to listen

ሰናይት መብራህቱ፤ የሥነ ጥበብ ሕይወት ሕልሟ ከአገር ቤት ውዝዋዜና እንጉርጉሮ እስከ ኤልቪስ ፕሪስሊ የፊልም ትወና የዘለቀ ነው። ከውልደት እስከ ስደት ያለ የሕይወት ጉዞዋን አሰናስላ ታወጋለች።


ሰናይት የተፀነሰችው መቀሌ ሲሆን፤ ለውልደት የበቃችው ጨርጨር - ራያ ሴት አያቷ ዘንድ ነው።

የሕይወት ጥላ ሆኗት ለዕቅፍ በበቃች በአንድ ወሯ ግጭት ተቀሰቀሰ።

ከእናቷ ጋር ከራያ ወደ መቀሌ ተመለሰች።

ከፍ ብላም አፈር መፍጨት፣ ፊደል መቁጠር ጀመረች።

ሲልም ጆሮዎቿ በአገርኛ ሙዚቃ ተቃኙ። ትከሻዎቿ በባሕላዊ እስክስታ መርገድ ያዙ።
Community
Senayt Mebrahtu (R). Source: S.Mebrahtu
ጣፋጭ የልጅነት ሕይወቷ ግና ከአንድ አሠርት ዓመት በላይ ለመቀሌ አልታደለም።

ዳግም ሌላ ግጭት ተፈጠረ። አፍላ የልጅነት ሕይወቷ ለካርቱም ስደት ተዳረገ።
Community
Senayt Mebrahtu. Source: S.Mebrahtu
የሱዳን ሕይወቷ ባሕር ማዶ ባሉ ኢትዮጵያውያን ከሚረዳ "ዓባይ" ትምህርት ቤት ጋር በቀለም ተቆራኘ። 

የቀለም ትምህርቷን ከሙዚቃና ድራማ ጋር አዋድዳ ቀጠለች።

ሕይወት በአገረ አውስትራሊያ   

የሰናይት የአውስትራሊያ ሕይወት ጅማሮ ግርታን የተላበሰ ነበር።

ከቋንቋ፣ ባሕልና የአኗኗር ዘይቤው ይልቅ የአገሯን ሰዎች ፈልጋ ማግኘት፤ ሌላው ቀርቶ በቆዳ ቀለም የሚቀራረቧትን እንኳ እንደ ልብ ማየት አለመቻል አዋኪ ስሜትን ፈጠረባት።

የትምህርት ቤት ሕይወቷ ግና በአንዲት ጥያቄ የጥበበ ዕጣ ፈንታዋን ለመቅረፅ በቃ።

ጠያቂዋ መምህርቷ ነበሩ።

ጥያቄያቸውም " ስታድጊ ምን መሆን ትፈልጊያለሽ?" የሚል ነበር።

የሰናይት ምላሽ "ተዋናይት" ሆነ።

ቁም ነገረኛዋ መምህርት የቲአትር ኩባንያ ማፈላለግ ጀመሩ።

ቀናቸው። 

ሰናይት ከቲአትር ኩባንያው ጋር ተቀላቀለች።   

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ምርጫዋ ውስጥ ቲአትርን አካተተች።

የእናቷ ድጋፍ ታከለበት። የመንፈስ ብርታትን አገኘች።

የዩኒቨርሲቲ ሕይወቷም በፈጠራ ትምህርት መታነፅ ቀጠለ።

20 ተዋናዮችን ለላቀ የጥበብ መድረክ የሚያወዳድር ዕድል ገጠማት።

ከ800 አመልካቾች ውስጥ ማጣሪያውን ካለፉት 40 ታሳቢዎች ውስጥ አንዷ ሆነች።

ሆኖም ከ20ዎቹ ውስጥ ሳትካተት ቀረች።

ቀጣዩን ዓመት በትወና የቲአትር ጥናት ትምህርት ቀስማ በቀዳሚ ዲፕሎማ ተመረቀች።

የሰናይት የትወና ሕይወት በረከት የመጣው በአውስትራሊያዊቷ ተዋናይትና ፀሐፌ ተውኔት ሳሊ ማኬንዚ "Scattered Lives" አጭር ተውኔት አማካይነት ነው።

ተውኔቱ የቀረበው ሰናይት በታደመችበት አንድ የምረቃ ቲአትር ዝግጅት ወቅት ነበር።

ጭብጡም የስደተኞችን ሕይወት የሚያንፀባርቅ ነው።

የራሷን የሕይወት ገፅታ በማኬንዚ የብዕር ቀለም ፍስሰት መድረክ ላይ ያየችው ሰናይት ሳሊ ዘንድ ቀርባ ምስጋናዋን አቀረበች።

የሙያ ጉዞ ምኞቷንም ገለጠች።

ሳሊ በሁለት ተዋናዮች በገጠሪቱ ኩዊንስላንድ ላሉ ተማሪዎች የሚተወን "A Safer Place" አጭር ተውኔት እነሆኝ አለቻት።
Community
Senayt Mebrhatu (R). Source: S.McKenzie
እንዲያ ባለ ሁኔታ ሰናይት ከአንዲት አውስትራሊያዊት የመድረክ ተዋናይት ጋር ሆና ወደ ትወና ሕይወት ዘለቀች።
ተዋናይት ሰናይት መብራህቱ፤ ከመድረክ ወደ ቴሌቪዥን ድራማ

ተዋናይት ሰናይት መብራህቱ፤ ከመድረክ ወደ ቴሌቪዥን ድራማ



   

 

 

 


Share