አውስትራሊያ ውስጥ የተገለገሉበትን መኪና እንደምን መሸጥ እንደሚችሉ

Australia Explained - Selling your Car - Young Man Taking a Picture of His Car

Credit: XiXinXing/Getty Images

Get the SBS Audio app

Other ways to listen

አውስትራሊያ ውስጥ አገልግሎት ላይ የዋለ መኪናን መሸጥ እንደሚኖሩበት አካባቢ ይለያያል። የመኖሪያ ክፍለ አገርዎ ወይም ግዛት የትም ይሁን የት መኪናዎን ከዕውክታ በራቀ መልኩ ለመሸጥ የሚከተለው የማጣሪያ ዝርዝር ያግዝዎታል።


አንኳሮች
  • አውስትራሊያ ውስጥ ሶስት የመኪና መሸጫ መንገዶች አሉ፤ ግለሰብ-ለግለሰብ, በመኪና መሸጫ ድርጅቶች ወይም በጨረታ አማካይነት።
  • መኪናዎን በግልዎ በሚሸጡበት ወቅት የመሸጫ ዋጋ፣ ለሽያጭ ከማቅረብዎ በፊት ጥገና ያስፈልገው እንደሁ፤ እንዲሁም በተወሰኑ ክፍለ አገራት የመኪና ደህንነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀትን ከግምት ውስጥ ማስገባት ያሻል።
  • መኪናዎን ከሸጡ በኋላም በተሽከርካሪ ምዝገባ ባለስልጣን በኩል የባለቤትነት ምዝገባን ማስተላለፍ ግዴታ ነው።
አውስትራሊያ ውስጥ አገልግሎት ላይ ለዋሉ መኪና ሻጮች ትልቅ ተደራሽ ገዢዎች አሉ።

በቅርቡ እንደገለጠው አገልግሎት ላይ የዋሉ መኪናዎች ገበያ መጠን ከአዲስ መኪና ገበያ ሶስት እጥፍ ያህል መጠነ ሰፊ ነው።

ይሁንና መኪናዎን ለሽያጭ ማቅረብ የሚቻልዎት እንደምን ነው?

በመጀመሪያ ከውሳኔ ላይ መድረስ ያለብዎት መኪናዎን በግል ወይም ሕጋዊ ፈቃድ ባለው መኪና ሻጭ ወይም በጨረታ ቤት መሸጥ ይፈልጉ እንደሁ ስለመሆኑ፤ በኒው ሳውዝ ዌይልስ ፍትሐዊ ንግድ የድንጋግጌ ግንኙነት ዳይሬክተር የሆኑት ካቲ ታውንሴንድ ልብ ያሰኛሉ።
Australia Explained - Selling your Car - Automobile For Sale
Credit: Alan Powdrill/Getty Images
“ለመኪና ሻጭ ባለቤት የሚሸጡ ከሆኑ የመኪና ሻጭ ባለቤቶች ከወጪዎቻቸው፣ የትርፍ መጠንና ለቀጣዩ ገዢ ካሉባቸው ግዴታዎች አኳያ የሚያገኙት ዋጋ ዝቅ ያለ ይሆናል። ከጨረታ ቤት ወስደው የሚሸጡ ከሆነ፤ ከሽያጭ ዋጋው ላይ በአብዛኛው ከ10 እስከ 15% የሚደርስ የጨረታ አገልግሎት ክፍያ መክፈልን ከግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርብዎታል” በማለት።

የጨረታ ቤት ጥንታዊ የሆኑና የተመረጡ መኪናዎች ገዢ ለሆኑ ተመራጭ ሲሆኑ፤ የመኪና ሻጭ ባለቤቶች ግና አሮጌ መኪናዎን በአዲስ ለመለወጥ ወይም የመኪና ሽያጭዎ ሂደት ውክልናን ለመስጠት ጥሩ አማራጭ ናቸው።

የግለሰብ-ለ-ግለሰብ ሽያጮች በአብዛኛው የኦንላይን ማስታወቂያ መድረክ በሆነው እንደ ፌስቡክ ገበያ ወይም ለግል ሻጮች አዘቦታዊ የሆኑ የግል መሸጫ ሥፍራዎች ተመራጭ ናቸው።

ወ/ሮ ታውንሴንድ መኪናዎን በግል በሚሸጡበት ወቅት ከግምት ውስጥ ሊያስገቧቸውና ይዘዋቸው ሊገኙ ስለሚገቡ የወረቀት ሥራዎች በግርድፉ ሲያመላክቱ፤
Australia Explained - Selling your Car - on phone line
concerned Asian Chinese mature woman comparing financial bill statement with bank on phone line Credit: Edwin Tan /Getty Images
“ማንኛውም ገዢ የመኪና ምዝገባ ሰነዶችን ማረጋገጥ፤ ሲልም፤ እርስዎ የመኪናው ባለቤት ስለመሆንዎ የመንጃ ፈቃድዎን ሳይቀር ሊጠይቅዎት ይችላሉ። እንዲሁም እንደ የመሳሰሉ ዝርዝር ነገሮችን ሊጠይቁዎት ይችላሉ። መኪናዎ ምናልባትም ዕዳ እንዳለበትና እንደሌለበት በ በኩል ለማጣራት ሲሉ" ብለዋል።

የግል ሽያጭ ጥቆማዎች

የኦንላይን መድረክ መኪና ሽያጮች ሸማቾች ግብይት ሥራ አስኪያጅ፤ ካራ ፋኢላ፤ የመኪና ምዝገባ ስኬት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖዎችን ሊያሳድሩ የሚችሉ ቁልፍ ጉዳዮችን ይጋራሉ።
  • ግልፅነት፤ ማናቸውንም ዓይነት ሳንካ አካትቶ፤ የመኪናዎ ታሪክና አያያዝ ሁኔታ “በምርመራ ሂደት ለገዢነት ከመጡ ሸማቾች ጋር በአካል በሚገናኙበት ወቅት ካልተጠበቀ አሸማቃቂ ክስተት ይታደግዎታል።”
  • የእርስዎ ለሸማቾች ምላሽ የመስጫ ጊዜ፤ “ሳይዘገይ በወቅቱ ለጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ጠቃሚ ነው […] ይህንንም ማድረግ ለእርስዎ ጥቅም አለው፤ ስለምን የእርስዎን መኪና ለመግዛት የጠየቀ ሸማች ሌሎች መኪናዎችንም ለመግዛት ይጠይቃልና። እናም አጋጣሚውን መጠቀምዎን እርግጠኛ ይሁኑ።”
  • ድርድርና ዋጋ ትመና፤ “የዋጋ ትመና በአብዛኛው በሸማቾች ፍላጎት የሚመዘን ይሆናል። ፍላጎት ለማሳደር የመኪናዎን ዋጋ ከእውነተኛ ገበያ ዋጋ ጋር ተቀራራቢ ለማድረግ ይሞክሩ […] እንዲሁም ከቻሉ፤ ሊቀበሉት የሚችሉትን ዝቅተኛ ዋጋ ተብሎ የሚታወቀውን ለድርድር የሚሆን መጠነኛ ክፍተት ይተው።”
በምዕራብ አውስትራሊያ የሮያል አውቶሞቢል ክለብ ተሽከርካሪዎችና ነዳጅ ሥራ አስኪያጅ አሌክስ ፎረስት፤ ከሽያጭ በፊት የመለዋወጫ ዕቃዎች በዋጋ ትመናና ድርድሮች ላይ የሚጫወቱት ሚና እንዳለ ይናገራሉ።
በአብዛኛው፤ በማስታወቂያዎች ላይ ትመለከታለችሁ። በሸማች ላይ ሊገዙት ስለሚችሉት መኪና ጥሩ ስሜት ለማሳደር። እንደምታውቁት፤ መኪናው ተጠግኖ፣ አዳዲስ ጎማዎች ተገጥመውለት።
አሌክስ ፎረስት
“ሁሉም ተጨማሪና አማራጭ ታካዮች መኪናው ላይ ረብ ያለው ዋጋ አይጨምሩም። በተለይም፤ ገዢው እርስዎ ያከሉበትን ያልወደደ ከሆነና መኪናውን ቀደም ሲል ወደ ነበረበት መመለስ የሚሻ ከሆነ” በማለት።
Australia Explained - Selling your Car -  woman driving a car
Australia Explained - Selling your Car - woman driving a car Credit: FG Trade/Getty Images
ፍላጎት ያላቸው ሸማቾች መኪናዎን በአካል ተገኝተው መመርመር ይፈልጋሉ፤ ይሁንና የተወሰኑ ሰዎች የማያውቋቸው ሰዎች ቤታቸው እንዲመጡና መኪናቸውን ለሙከራ እንዲነዱባቸው አይሹም።

ወ/ሮ ፋኢላ ይህንን በተዘዋዋሪ እንደምን መከወን እንደሚቻል አስተያየታቸውን ሲያጋሩ፤

“ከሸማች ጋር ሰዎች በዙሪያ የሚገኙበት፤ ለምሳሌ እንደ ገበያ መኪና ማቆሚያ የመሰለ ሕዝባዊ ሥፍራ ላይ መገናኘት ይችላሉ።

“መኪናዎን ለሙከራ መንዳትን በተመለከተም መኪናዎን በሚነዱበት ወቅት እነሱ የሚነዱትን መኪና ቁልፎች ወይም የመንጃ ፈቃድ በዋስትናነት መያዝ ይችላሉ። እንዲሁም፤ በሙከራ መንዳት ወቅት አብረዋቸው ከመንገደኛ ወንበር ላይ ተቀምጠው መሔድም ይችላሉ” ይላሉ።

ሆኖም፤ አማራጭ ማሻሻያና መጠነኛ ለውጥ ማድረጊያዎች ሁሌም መኪናን ለመሸጥ አስፈላጊ ወይም ብልህ አማራጭ አይደሉም።
Mechanic fixes engine
Australia Explained - Mechanic fixes engine Credit: Reza Estakhrian/Getty Images

ቅድመ-ሽያጭ እና ድኅረ-ሽያጭ መሥፈርቶች

በሚኖሩበት ከፍለ አገር/ግዛት መኪናዎን ከመሸጥዎ በፊት መኪናዎ ማሟላት የሚገባው ቅድመ ሁኔታዎች የሚያሟላ መሆን አለመሆኑን ያረጋግጡ።

ቪክቶሪያ ውስጥ፤ ለምሳሌ የመኪና ባለቤትነትን ለሌላ ከማስተላለፍዎ በፊት የመኪናዎ ጎዳና ላይ የመሽከርከር ብቃት ምስክር ወረቀትን መያዝ ግድ ይላል። ይሁንና ምዕራብ አውስትራሊያ ውስጥ ግና ይህ ግዴታ አይደለም።

“እናም፤ የመኪና ምርመራን አስመልክቶ በተለያዩ የአውስትራሊያ ክፍለ አገራት ውስጥ ሁነኛ ልዩነቶች አሉ”

“በሌላም በኩል የመኪና መካኒካዊ ሁኔታ ምርመራን በተመለከተም ውክልና አልተጣለባቸውም፤ ሆኖም አገልግሎት ላይ የዋሉ መኪና ሸማቾች ከግምት ውስጥ እንዲያስገቧቸው በብርቱ ይመከራል” በማለት ያሳስባሉ።

በመጨረሻም፤ መኪናዎን ከሸጡ በኋላ ሶስት ሊከውኗቸው የሚገቡ ቁልፍ ጉዳዮች አሉ፤
  • የኢንሹራንስና የመንገድ ዳር አገልግሎት ሰጪዎችን ያነጋግሩ
  • የቀድሞ አገልግሎት አካውንትዎ ወደ አሁኑ መኪናዎ መሸጋገሩን ያረጋግጡ፤ እንዲሁም
  • በክፍለ አገርዎ/ግዛትዎ ላለው የሞተር ምዝገባ ቢሮ ያሳውቁ።
ኒው ሳውዝ ዌይልስ ውስጥ፤ ለምሳሌ ያህል የመኪና ለውጥዎን ለአገልግሎት ኒው ሳውዝ ዌይልስ ማሳወቅ ይኖርብዎታል።

“መኪናዎን እንደሸጡ ይህን በተቻለ ፍጥነት መከወኑ አስፈላጊ ነው፤ ስለምን በአዲሱ ገዢ ላይ የተጣሉ ቅጣቶችን ከመቀበል ያድንዎታልና” በማለት የኒው ሳውዝ ዌይልስ ፍትሐዊ ንግድ ተወካይዋ ታውንሴንድ ያስረዳሉ።
Car repairman giving car keys to customer
Car repairman giving car keys to customer after success car repairing in garage Source: Moment RF / thianchai sitthikongsak/Getty Images
እናም ልብ ይበሉ፤ ሰነዶችና የባለቤትነት ለውጥ፣ የመኪና ሽግግር መሥፈርቶች በመላ አገሪቱ የተለያዩ ስለመሆናቸው ሲያመላክቱ፤

“የሚኖሩበት ክፍለ አገር መሥፈርቶች ምን እንደሆኑ ያጣሩ። ከክፍለ አገር ክፍለ አገር ይለያያሉና። ይሁንና በአብዛኛው፤ የእርስዎ የተሽከርካሪ ምዝገባ ባለስልጣን ማንም ይሁን ማን ሊያሳውቋቸው ይገባል። ያም መደበኛ መሥፈርት ነው” ብለዋል።

መኪናዎን ሸጡ?

እንኳን ደስ ያለዎት! አውስትራሊያ ውስጥ ነደሚኖሩበት አካባቢ ቀጥለው ሊከውኑ የሚገባዎትን እነሆ።

Share