ለተማሪዎች የሚሆኑ መኖሪያ ቤቶች ምን ዓይነት ናቸው?

Group of four young adults relaxing on patio outside house with food and drink

Multi racial group of friends enjoying lunch, talking and smiling on wooden decking Credit: JohnnyGreig/Getty Images

Get the SBS Audio app

Other ways to listen

አውስትራሊያ ለባሕር ማዶ ትምህርት በጣሙን ዝነኛ ከሆኑት መዳረሻዎች አንዷ ናት። እንዲሁም በአሁኑ ወቅት የኪራይ ቤት ፈልጎ ለማግኘት አዋኪ ከሆኑባቸው ሥፍራዎች ውስጥም ትገኛለች። ወቅቱ በተለይም ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ለተማሪዎች በጣሙን ጠቃሚ የሚሆኑ የመኖሪያ ቤት አማራጮችን መገንዘቢያ ነው።


አንኳሮች
  • መኖሪያ ቤት ሲያፈላልጉ በቅድሚያ በጀትዎንና የአኗኗር ዘዬ ፍላጎቶችዎን ይለዩ
  • በዩኒቨርሲቲ የማስታወቂያ ሠሌዳዎችና የማሕበራዊ ሚዲያ ገፆች እገዛን ይጠይቁ
  • በዩኒቨርስቲዎ ወይም ኮሌጅዎ አቅራቢያ ለተማሪዎች ተብለው የተገነቡ የመኖሪያ ቤት አማራጮችን ይመልከቱ
  • በዩኒቨርሲቲ ባለቤትነት ስር ያሉ የመኖሪያ ቤቶች ድጋፍን እያገኙ ባለበት ወቅት ከአዲሱ ከተማዎ ጋር ለመላመድ አንዱ ትልቅ መንገድ ነው
የመኖሪያ ቤት ፍለጋዎ የት እንደሚማሩ ማረጋገጫ እንዳገኙ ወዲያውኑ መጀመር ይኖርብዎታል። መኖሪያ ቤትዎ፣ ከበጀትዎ፣ ቀዬዎና የአኗኗር ዘይቤዎ ጋር የሚስማማ መሆን አለበት። ጥቂት በጣም ታዋቂ አማራጮችን እነሆ።

መቆያ ቤቶች

መቆያ ቤቶች የቤተሰብ ቤቶች ሆነው ተማሪዎች የመኝታ ክፍልና ምግብ እያገኙ የሚኖሩባቸው እንደሆኑ የአውስትራሊያ ጥናት ዳይሬክተር ዎጅቴክ ዋውርዚንስኪ ይናገራሉ። በርካታ ተማሪዎች በመጀመሪያ ጥቂት ወራቶቻቸው የተለያዩ ዓይነት መኖሪያ ቤቶችን እንዲያገኙ የረዱ ናቸው።

“የመቆያ ቤቶች በአብዛኛው የአውስትራሊያን ባሕል መልመድ በሚፈልጉና ለብቻቸው ኖረው በማያውቁ ተማሪዎች ይያዛሉ” ሲሉም ያስረዳሉ።

የመቆያ ቤቶች አማካይ ሳምንታዊ የኪራይ ክፍያ $350 ነው። እንደ እና የመሳሰሉ የተማሪዎች ድጋፍ ኤጄንሲዎችን ከአስተናጋጅ ቤተሰብ ጋር ያገናኝዎታል።

ዓላማ-ሠር የተማሪ መኖሪያ

ዓላማ-ሠር የተማሪ መኖሪያ በፍጥነት እየተስፋፋ ያለ መስክ ነው። በባለ ሙያተኞች የሚተዳደሩት የተማሪዎች መኖሪያ አፓርትመንቶቹ የቤት ኪራይን ጨምሮ ሌሎች ክፍያዎችንና ጥገናዎችን በማካተት የሚንቀሳቀሰው በሥርዓተ ንግድ ነው።

እኒህን የመሳሰሉቱን በከፊል በመኖሪያ ቤት ቁሳቁሶች የተመሉ የተማሪዎች አፓርትመንቶችን በሰማይ ጠቀስ ፎቆች ወይም ግዙፍ ሆነው በተገነቡ ዋነኛ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ኮሌጆች ወይም የሕዝብ ትራንስፖርት ባሉባቸው ሥፍራዎች ያገኛሉ።

የክፍያ መጠኑ እንደ ደባሎችዎ የሚወሰን ሲሆን ከ $280-350 ያህል ሊያስከፍልዎት ይችላል።

እንደ , እና የመሳሰሉ ታዋቂ ድረገፆች የተማሪ መኖሪያ ማመልክቻዎችን ያስተናግዳሉ። እንዲሁም በተማሪ ድጋፍ ኤጄንሲ በኩል ማመልከት ይችላሉ።
young asian woman studies with laptop from home
Credit: Cavan Images/Getty Images

የደባል መኖሪያ

ተማሪዎች ወደ የሚማሩበት አገር ከዘለቁ በኋላ፤ በአብዛኛው የደባል መኖሪያ ቤትን ያፈላልጋሉ፤ የደባል ቡድኖቻቸውን ያቋቋማሉ።

የደባል መኖሪያ አብዛኛዎቹ ነዋሪዎች በቋሚነት ከሚኖሩባቸው የኪራይ ቤት ገበያ ጋር የተያያዘ ሲሆን፤ የቤት ወጪዎችን በደባሎቹ ቁጥር ልክ ይከፋፈላሉ።

የእዚህ ዓይነቱ እፎይታ ባለው መልክ ወጪዎችን መጋራትና በራስ የመወሰን የአኗኗር ስምምነት በብዙዎች ዘንድ የተለመደና ተወዳጅ ነው።

ሳምንታዊ የኪራይ ክፍያ እንደ መኖሪያ ቀዬውና ወቅቱ ይለያያል።

, እና ከተወሰኑቱ ታዋቂ የደባል መኖሪያ ድረገፆች ውስጥ ተጠቃሾች ናቸው።

የሲድኒው ኤስ ኤም አሚኑል ኢስላም ሩብሌ፤ የማኅበረሰብዎን አውታረ መረቦችና የማኅበራዊ ሚዲያ ቡድናት መጠቀም የደባል መኖሪያ ቤትን ለማግኘት አንዱ ቀላሉ መንገድ እንደሆነ ይጠቅሳል።

አሚኑል፤ ዓለም አቀፍ ተማሪዎች ጥራት ካለው አኗኗር ይልቅ ስጋታቸው የወቅቱን የኪራይ ቀውስ ተቋቁሞ ማለፉ ላይ የሚያተኩሩ መሆኑን ተረድቷል።
ከባንግላዴሽ በዓለም አቀፍ ተማሪነት የመጣው አሚኑል፤ በቤት ኪራይ ፍለጋ የሚቸገሩ ተማሪዎችን ከአከራዮች ጋር ለማገናኘት አንድ የፌስቡክ ቡድን ይመራል።

በግኝቱ መሠረት በርካታ አከራዮች ቤቶቻቸውን ትምህርታቸው ላይ ለሚያተኩሩ ተማሪዎች ለማከራየት ደስተኞች መሆናቸውን ተገንዝቧል። እንደ አከራዮቹ አባባል እንዲህ ያሉ ተማሪዎች "ችግሮችና ራስ ምታትን" አይፈጥሩም።
በርካታ ተከራዮችን የሚሹ የግል ቤት አከራዮች አሉኝ። እንዲሁም፤ አያሌ የቤት ኪራይ ፈላጊ ተማሪዎችም አሉኝ። እናም፤ ላገናኛቸው እሞክራለሁ፤ አብዛኛውን ጊዜያት በጥሩ ሁኔታ ይሰምራል።
ኤስ ኤም አሚኑል ኢስላም ሩብሌ
አሚኑል አዲስ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ማኅበራዊ ቡድናትን እንዲቀላቀሉ ያበረታታል። .

“እርግጥ ነው፤ ሊሎች ከጥቂት ወራት በፊት ቤት ፍለጋ ሲቸገሩ የነበሩ ተማሪዎችም እገዛ ሊያደርጉ ይገባል” ሲልም ይመክራል።

የዩኒቨርሲቲ ማስታወቂያ ሠሌዳዎችን ስለ መመልከትና በራስ ቋንቋ እርዳታን ስለ መጠየቅ ሲያመላክትም፤

“ይሂዱና በራስዎ ቋንቋ 'አዲስ ነኝ፤ እርዳታን እሻለሁ' ብለው ይፃፉ። ማንኛውም የራሱን ቋንቋ ማስታወቂያ ሠሌዳ ላይ ተፅፎ ያየ ሰው በአብዛኛው ምን እንደሆነ ለማወቅ ያንብበዋል” ብሏል።
SG StudentAccommodation
A front-view shot of a young university student standing proud with a smile, she is wearing casual clothing and looking at the camera. Credit: SolStock/Getty Images

በዩኒቨርሲቲ-ባለቤትነት ስር ያሉ መኖሪያዎች

በዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ወይም በአቅራቢያው በርካታ በዩኒቨርሲቲ ባለቤትነት ስር ያሉ የኮሌጅ መኖሪያዎችና አፓርትመንቶችን ፈልገው ማግኘት ይችላሉ። የዩኒቨርሲቲ መኖሪያዎች በአብዛኛው ለተማሪዎች በጣሙን ማኅበራዊና አጋዥ አማራጮችን ይቸራሉ።

ምክትል ቻንስለር ፕሮፌሰር ሳሊ ዊለር (የአውስትራሊያ ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲ ዓለም አቀፍና ኮርፖሬት)

“እንደማስበው ከሆነ ቀደም ሲል አውስትራሊያ ውስጥ ያልተማረ ሰው የዩኒቨርሲቲ መኖሪያ ቤቶችን አስመልክቶ በትኩረት ሊያስብ ይገባል' ብለዋል።
ከአዳዲስ ሰዎች ጋር ለመገናኘትና ራስዎን ከአካባቢው ጋር ለማዋሃድ በጣሙን ጥሩ መንገድ ነው፤ እንዲያም ሆኖ ድጋፍ አይለይዎትም።
ፕሮፌሰር ሳሊ ዊለር
ፕሮፌሰር ዊለር፤

"የኮሌጅ መኖሪያዎች ምግቦችን፣ ደኅንነት የተመላባቸውን መኝታ ክፍሎች፣ የቀለም ትምህርት ድጋፍና የዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ መዝናኛ ሥፍራዎችን ይቸራሉ።"

“በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች አንድ ወይም ሁለት ከዩኒቨርሲቲ ጋር የተያያዙ የኮሌጅ መኖሪያዎች አሏቸው።”

“ለምሳሌ ያህል፤ በአብዛኛው የስፖርት ተቋማትን ለመጠቀም ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር ስምምነት አላቸው” ብለዋል።
SG StudentAccommodation
A diverse group of students in their 20's walking down some steps on campus laughing and talking to each other. Credit: SolStock/Getty Images
አንድ የኮሌጅ መኖሪያ ክፍል ኪራይ ዋጋ እንደ ዩኒቨርሲቲዎቹ ይለያያል። ምናልባትም በሳምንት እስከ $700 ሊከፍሉ ይችላሉ፤ ሆኖም ማስታወስ ያለብዎት ሁሉንም አገልግሎቶች ያካተተ መሆኑን ነው።

በተቃራኒው ግና፤ የጠቅላላ ዩኒቨርሲቲ መኖሪያ ሙሉ በመሉ የተሟላ፣ በከፊል የተሟላ ወይም በራስ የሚሟላ መኝታ ክፍል አማራጮች አሏቸው። የተቋማቱን አገልግሎቶችና ማኅበራዊ ዕድሎችንም እየተጠቀሙ ራስዎን ችለው መኖር የሚሹ ከሆነ፤ እንዲያም ሆነ ርካሹ አማራጭ ነው።

ዩኒቨርሲቲዎች የሁለቱም ዓይነት የመኖሪያ ቤት ማመልከቻዎችን ተቀብለው ያስተናግዳሉ። የተወሰኑት የእነሱን የመጠይቅ መስፈርቶች ሲቀበሉ ዋስትናን የሚሰጡ ሲሆን፤ ሌሎች ወደ አውስትራሊያ ከመዝለቅዎ በፊት ሌላ ማመልከቻ እንዲያስገቡ ይጠይቃሉ።

እንዲሁም፤ የተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች የዳታ ሠንጠረዥ ከዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውጪ ያሉ መኖሪያዎች በመማር ላይ ባሉና ለመማር ወጥነው ላሉ ተማሪዎች ተደራሽ በማድረግ ራሳቸው ይከውናሉ።
ተጨማሪ ምንጮች

(የአውስትራሊያ መንግሥት)

Share