ወደ ክፍለ አገር ሔዶ ለመኖር ያሉ መሥፈርቶች ምንድን ናቸው?

SG Moving Interstate - A young woman is packing her moving boxes

Settlement in a new country is a significant process, so moving interstate can feel like settling twice. Credit: Catherine Delahaye/Getty Images

Get the SBS Audio app

Other ways to listen

በየዓመቱ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ አውስትራሊያውያን ለሥራ፣ ለትምህርት፣ በአኗኗ ዘዬ ምርጫ፣ በቤተሰብ ጉዳይ ወይም የተሻለ የማኅበረሰብ ድጋፍን ለማግኘት ሲሉ ከክፍለ አገር ወደ ክፍለ አገር ይዛወራሉ። በአገሪቱ ውስጥ ሕጎች፣ ደንቦችና የአገልግሎት አቅርቦቶች ሊለያዩ ይችላሉና ዝውውርዎ እንቅፋት እንዳያገኘው ዝርዝር የክዋኔ ማረጋገጫ አጋዥ ሊሆንዎት ይችላል።


አንኳሮች
  • ከክፍለ አገር ወደ ክፍለ አገር ተዘዋሮ መላመድ ብርቱ ጫና አለው
  • የተለያዩ ከፍለ አገራትና ግዛቶች የየራሳቸው ሥርዓቶች፣ አገልግሎቶችና ሕጎች አሏቸው
  • ወደ ክፍለ አገር መዛወር ያልጠበቁ ወጪዎችን ሊያስከትል ይችላል
  • እንቅፋት አልባ ዝውውር እንዲሆንልዎ ዝውውር ከማድረግዎ በፊት ምርምር ማድረግ ያግዛል
በመላ አገሪቱ ከክፍለ ወደ ክፍለ አገር የሚዘዋወሩ ሰዎች ቁጥር ያለማቋረጥ እየጨመረ ነው። እንደ አውስትራሊያ ስታቲስቲክ ቢሮ ምልከታ፤ ከቶውንም ዝውውሩን የሚሹቱ አውስትራሊያ ከተወለዱት ይልቅ ውልደታቸው ባሕር ማዶ የሆኑቱ መሆናቸው ነው።

ይሁንና፤ ልክ አዲስ አገር ሔዶ የመኖር ያህል ወደ ክፍለ አገር መዛወርም ብርቱ የመላመድ ሂደትን ያቀፈ ነው። የተለያዩ ክፍለ አገራትና ግዛቶች የየራሳቸው የሆኑ ሥርዓቶች፣ አገልግሎቶችና ሕጎች እንዳላቸው ሁሉ።
የክፍለ አገር ዝውውርን እንቅፋት አልባና የተለሳለሰ ለማድረግ፤ ከግምት ውስጥ የሚያስገቧቸውን ዘርፈ ብዙ የክዋኔ ማረጋገጫ ዝርዝሮችን ያካተቱና የተወሰኑ ፍንጮችን እነሆ።

አግባብ ላላቸው ባለስልጣናት አድራሻዎን ያሳውቁ

ወደ ክፍለ አገር መዛወር ማለት ለተለያዩ መንግሥታዊ ድርጅቶች፣ ባንኮች፣ ለሚገኙበት ክፍለ አገር ወይም ግዛት ባለስልጣንና ሌሎች አገልግሎት ሰጪዎች አድርሻዎን ማስታወቅ ይኖርብዎታል።

"ሰዎች አድራሻቸውን ለጓደኞቻቸው ብቻ ሳይሆን ለባንካቸው፣ ምናልባትም ድጎማ ተቀባይ ከሆኑ ለሴንተርሊንክ ማስታወቅ ይኖርባቸዋል። በተለየ የቪዛ ዓይነት ያሉ ከሆነም ሲሉ የሠፈራ አግልግሎቶች ሰጪ የሆነው የሕዝብ ጉዳዮች ሥራ አስኪያጅ ሎሪ ኖዌል ያስረዳሉ።
ደብዳቤዎችዎ ከአሮጌ አድራሻዎ ወደ አዲሱ አድራሻዎ እንዲመጡልዎት አድራሻዎን ቀደም ብለው ማሳወቁ ጠቀሜታ አለው።
የAMES አውስትራሊያ፤ የሕዝብ ጉዳዮች ሥራ አስኪያጅ ሎሪ ኖዌል
new apartment selfie time
a young couple unpack their belongings as they settle into their new loft apartment . Credit: E+
አብዛኛዎቹን እኒህ ለውጦች በቀላሉ በኦንላይን መከወን ይችላሉ፤ ጥረትና ጊዜዎን ይቆጥብልዎታል።

አውስትራሊያ ውስጥ የምርጫ ድምፅ መስጠት ግዴታ እንደሆነም ልብ ማለቱ ጠቃሚ ነው። ሁሌም መኖሪያዎን በለወጡ ቁጥር አለያ ስምዎ ይፋቃል፤ ምርጫ መምረጥ አይችሉም።

ዝውውርዎን ለአውስትራሊያ ምርጫ ኮሚሽን ያስታውቁ፤ በአዲሱ ክፍለ አገርዎ ለመምረጥ እንዲችሉ ምዝገባ ማካሔድዎን እርግጠኛ ይሁኑ። ለመምረጥ ብቁ ሆነው ሳለ ሳይመዘገቡ ቢቀሩ መቀጮ ሊያገኝዎት ይችላል።

የዝውውር በጀት

ከከፍለ አገር ወደ ክፍለ አገር መዘዋወር ያልተጠበቁ ወጪዎችን ያስከትላል።

ወጪዎቹም የትራንስፖርት፣ ጊዜያዊ ማረፊያ ቤት፣ ከመንጃ ፈቃድና የመኪና ምዝገባ ጋር የተያያዙ ሰነዶችን ለመለወጫ የሚወጡ ይሆናሉ።

ከሲድኒ ወደ ሜልበርን ለሙያዊ ሥራ የተዘዋወረችው ፓላቪ ታካር በዝውውር ወቅት ያልታሰቡ ወጪዎችን ለማስወገድ በጀት መመደብ አስፈላጊ እንደሆነ ምክረ ሃሳቧን ስትቸር፤

"ከአንድ ከፍለ አገር ወደ ሌላ ክፍለ አገር መሔድ ትልቅ ዝውውር ስለሆነ፤ ዝውውርን አስመልክቶ በጀት መመደብ ጠቃሚ ነው። በዝውውራችን ወቅት 10 ሺህ ዶላር ያህል ፈጅቶብናል" ብላለች።
SG Moving Interstate - desk with keys and documents
Flat lay of real estate concept ***These documents are our own generic designs. They do not infringe on any copyrighted designs. Source: iStockphoto / Rawpixel/Getty Images/iStockphoto
ወደ ሌላ ክፍለ አገር ከመዛወርዎ በፊት የክፍያ ለውጥ ይኖር እንደሁ የኢንሹራንስ ኩባንያዎችዎን አነጋግረው ያረጋግጡ።

የፕሪሚየምና አገልግሎት ሰጪዎች ሊለያዩ ይችሉ ይሆናል። እናም፤ በአዲሱ አድራሻዎ የእርስዎ ኢንሹራንስ ሽፋኖች ተመጣጣኝና ተገቢ ሆነው ያሉ መሆናቸውን ማረጋገጡ አስፈላጊ ነው።

የትምህርት አሠራሮችን ይመርምሩ

እርስዎ ወይም ልጆችዎ ለትምህርት ወይም ሰልጠና ትምህርት ቤት ተመዝግበው ከሆነ እራስዎን ከአዲሱ ክፍለ አገርዎ ሥርዓተ ትምህርት ጋር ያዛምዱ።

አውስትራሊያ የምትከተለው ብሔራዊ ሥርዓተ ትምህርት ያላት ቢሆንም በመላው ክፍለ አገራት የትምህርት ክፍለ ጊዜያት፣ የምስክር ወረቀቶችና የትምህርት ዓይነቶች ሊለያዩ ይችላሉ።

ምርምር ማድረግዎ እራስዎ ወይም የቤተሰብዎ አባላት ያላንዳች ዕንቅፋት ሽግግር እንዲያደርጉ ያግዛል።

የወሸባ ሕጎችን ልብ ይበሉ

አውስትራሊያ ከዓለም ጥብቅ የሆነ ለይቶ የማቆያ ሕጎች አሏት፤ እኒህም ወደ ክፍለ አገር በሚዘዋወሩበት ወቅት ግብር ላይ የሚውሉ ናቸው።

ተክሎች፣ የእንሰሳት ውጤቶችና የግብርና ቁሳቁሶች ሊበከሉ ስለሚችሉ የቀድሞ ሥፍራዎ ጥለዋቸው እንዲሔዱ ይመከራል። በተጨማሪ ለማወቅ ካሹ ከ ማግኘት ይችላሉ።

ከድጋፍ አውታረ መረቦች እገዛን ይጠቁ

ወደ አዲስ ክፍለ አገር መዛወር አስደሳችም አዋኪም ሊሆን ይችላል። የተወሰኑ ፍልሰተኞ ቤተሰቦች ከድጋፍ አውታረ መረቦች ጋር በመገናኘት ስለ አዲሱ የመኖሪያ ቀዬአቸው ምክርን ለመጠየቅ ከባሕላዊ የማኅበረሰብ ቡድናት ጋር መቀላቀልን ምቾት ሰጪ አድርገው ይወስዷቸዋል።

የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች እንዲሁ አካባቢውን ከሚያውቁቱ ግብራዊ ምክሮችን ለመጠየቅ፣ ማለፊያ ምንጮችና ረጂ ፍንጮችን ለማግኘት ጠቃሚ ናቸው።

ወ/ሮ ታካር የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ግብራዊ ምክሮችን ለማግኘትና ጫናዋን ለማቅለል ጠቃሚ ሆነው አግኝታቸዋለች።

"በመሠረቱ፤ ጥያቄዬን ፌስቡክ ላይ አወጣሁ፤ ሰዎች በርካታ አተያዮቻቸውን በማጋራት ቸር ሆነውልኛል። ለእኛ ለከተማ መቅርቡ ጠቃሚ ስለነበር ወደ ሩቅ ሠፈሮች ከመሔድ ለመታቀብ በቅተናል" ብላለች።
SG Moving Interstate - family packing moving boxes into car
Credit: Ariel Skelley/Getty Images

የሠፈራ አገልግሎቶች ሰጪዎችን ይጠቀሙ

ከማኅበረሰባዊ መድረኮች ባሻገር፤ የሠፈራ አገልግሎቶችና የፍልሰተኛ ማዕከላትም እገዛ እንደሚቸሩ አቶ ኖዌል ያስረዳሉ።

በክፍለ አገር ዝውውርዎ ወቅት የሠፈራ አገልግሎቶች ሰጪዎችና የፍልሰተኛ ማዕከላት ጠቃሚ ሽርካዎች ሊሆንዎት ይችላሉ።

እርዳታና ምክር ይቸርዎታል፤ የትጉምና አስተርጓሚ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ያግዝዎታል። እገዛቸው በተለይም የቋንቋ ችግር ላለባቸው ማለፊያ ድጋፍ ይሆናል።
መንግሥት ሕዝብ በነፃ የሚጠቀምባቸው የትርጉምና አስተርጓሚ አገልግሎት አሉት። ሰዎች በኦንላይም ሊጠቀሙባቸው ይችላሉ። ወደ አካባቢዎ ፍልሰተኛ ማዕከል ወይም ቪክቶሪያ ውስጥ AMES ዘንድ ከሔዱ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ እገዛን ይቸርዎታል።
ሎሪ ኖዌል፤ የሠፈራ አገልግሎቶች ሰጪ AMES አውስትራሊያ የሕዝብ ጉዳዮች ሥራ አስኪያጅLaurie

Share