አውስትራሊያ ውስጥ የድመት ባለቤት ኃላፊነት ምንድነው?

SG CAT Ownership 1.jpg

Keeping your pet cat contained indoors keeps them safe and protects wildlife too.

Get the SBS Audio app

Other ways to listen

ቤትዎ ውስጥ ድመት ያለዎት ወይም ለማሳደግ አስበው ያሉ ከሆነ፤ ኃላፊነት የተመላው የድመት ባለቤት መሆን የድመትዎን ደኅንነት ለመከባከብና የአውስትራሊያን አገር በቀል እንሰሳት ለመታደግ ይረዳል።


አንኳሮች
  • አውስትራሊያ ውስጥ 5.3 ሚሊየን የቤት ውስጥ ድመቶች አሉ
  • አውስትራሊያ ውስጥ ክቤት ውጪ እንዲዟር የተፈቀደለት እያንዳንዱ ድመት በዓመት 186 እንሰሳትን ይገድላል
  • ኃላፊነት የተመላው የድመት ባለቤት መሆን ድመትዎን ቤትዎ ውስጥ መንከባከብን ያካትታል
  • የአካባቢዎን ማዘጋጃ ቤት ያነጋግሩ ወይም ድረገፃቸውን ይጎብኙ
ድመቶች በአጫዋችነትና የተለያዩ ማለፊያ መቸር ይቻላቸዋል። ይሁንና አውስትራሊያ ውስጥ ከቤት ውጪ ያሉ ድመቶች የአገር በቀል እንሰሳት ሁነኛ አዳኞች ናቸው። ተዘዋዋሪነታቸውም ድመቶችን ለሕመምና ለመቁሰል አደጋ ተጋላጭ ያደርጋል።

ድመቶች የተስፋፋ ሉላዊ ባሕሎች አሏቸው። ዘመን ካሸመገለ የግብፃውያን አፈ ታሪክ አንስቶ፤ ከአሜሪካው ሰነፍ ድመት ጋርፊልድና በሁሉም ሥፍራ ደራሹ የጃፓኑ ሄሎ ኪቲ ክስተት የተከበረ ዝነኛ ባሕል አካል ሆነዋል።

ከ 5.3 ሚሊየን በላይ ድመቶች እንዳሏቸው ይገመታል።

ድመቶች በተፈጥሯቸው አዳኞች ናቸው። ተመራማሪዎች አውስትራሊያ ውስጥ እያንዳንዱ ድመት ባለቤቶቻቸው ለእማኝነት ሳይበቁ በአማካይ እንደሚገድል ይገልጣሉ።

ለማዳ ድመቶች በአውስትራሊያ ከሚያደርሷቸው ተፅዕኖዎች ባሻገር፤ በሚሊየን የሚቆጠሩ ባለቤት አልባ የውጭ ድመቶች በመላ አውስትራሊያ ይዘዋወራሉ።

በቻርልስ ዳርዊን ዩኒቨርሲቲ የዝንቅ ሥነ ሕይወት አማካሪና የዱር እንሰሳት ጥበቃ ፕሮፌሰር ሳራ ሌጌ ይህንኑ አስመልክተው ሲናገሩ፤

“እያንዳንዱ የቤት ውስጥ ለማዳ ድመቶች ባለቤትና ተከባካቢ የሆነ ሁሉ ልብ የሚለው ነው፤ ይሁንና አውስትራሊያ ውስጥ ባለቤት አልባ የውጭ ድመቶች አሉን፤ እነዚህ ድመቶች የሚኖሩት ሰው ላይ ጥገኛ ሳይሆኑ ነው። አብዛኛዎቹ ባለቤት አልባ የውጭ ድመቶች የሚኖሩት ከትናንሽና ትላልቅ ከተሞች ርቀው ባሉ ዱሮች ውስጥ ነው። እኒያ ዓይነቶቹ ባለቤት አልባ የውጭ ድመቶች ዘዋሪ ድመቶች ተብለውም ይጠራሉ" ብለዋል።
SG CAT Ownership 2.jpg
Cats make great companions and will happily let you live beside them.

ድመቶች በአውስትራሊያ የዱር ሕይወት ብርቱ ተፅዕኖ አላቸው

ፕሮፌሰር ሌጌ “ድመቶች ወደ አውስትራሊያ የዘለቁት በመጀመሪያው የእንግሊዝ መርከብ በ1788 ዓ.ም ነው። ባለቤት አልባ የውጭ ድመቶች ከሃያ በላይ ለሆኑ የአጥቢ እንሰሳትና ድመቶች ዝርያ ቁጥር መቀንስ አስባብ ሆነዋል" ብለዋል።

አውስትራሊያ ውስጥ በለማዳና ባለቤት አልባ የውጭ ድመቶች ልዩ በሆኑ የዱር ሕይወቶች ላይ በጥምር በሚደርሱ ተፅዕኖዎች በየቀኑ በድመቶች ከ 3.1 ሚሊየን በላይ አጥቢ እንሰሳት፣ 1.8 ሚሊየን በደረታቸው የሚሳቡ እንሰሳትና 1.3 ሚሊየን ወፎች ይገደላሉ። እንደ ፕሮፌሰር ሌጌ አባባል ተጨማሪ አገር በቀል እንሰሳትም ለአደጋ ተጋላጭ ናቸው።

“በድመቶች አስተዳደር ላይ ተገቢውን ቁጥጥር ካላደረን የአውስትራሊያ አገር በቀል እንሳሰሳት ላይ በመጪዎቹ አሠርት ዓመታት ተጨማሪ ጥፋቶች ሲደርሱ የምንመለከት ይሆናል። ባለቤት አልባ ከቤት ውጪ ነዋሪ ድመቶች ችግር እንደሆኑ እናውቃለን፤ ይሁንና ምንም እንኳ በባለቤቶቻቸው ቢቀለቡም የቤት ውስጥ ለማዳ ድመቶችም የዱር እንሰሳት ላይ ጥቃትን ያደርሳሉ። የቤት ውስጥ ለማዳ ድመቶች ወደ ውጪ ወጥተው እንዲዞሩ ከተፈቀደላቸው ከማደን አይገቱም። አደን የድመቶች ተፈጥሮ ስለሆነ። አያሌ የድመት ባለቤቶች ምናልባትም ይህን አያውቁም፤ ስለምን ድመቶቻቸው ከገደሏቸው እንሰሳት ውስጥ ወደ ቤት ይዘዋቸው የሚመጡት ከአምስት አንዱን ብቻ ነው፤ ከቶውንም አንዳንዶቹ ድመቶች አንዳችም የገደሏቸውን እንሰሳትን ወደ ቤት ይዘው አይመጡም” ሲሉ ፕሮፌሰረ ሌጌ አክለው ያስረዳሉ።
SG CAT Ownership 3.jpg
Feral Cat in Arid South Australia. Credit: Hugh McGregor

አውስትራሊያ ውስጥ ኃላፊነት የተመላበት የድመት ባለቤት መሆን ምንን ያካትታል?

ፕሮፌሰር ሌጌ በዱር ሕይወት ላይ የሚደርሱትን የድመቶች ተፅዕኖዎች ለመቀነስ ኃላፊነት የተመላበት ባለቤትነት የተሻለ መንገድ መሆኑን ሲናገሩ፤

“ድመትዎን ያስመዝግቡና ማይክሮቺፕ ያስገቡለት፤ እንዲያ ሲሆን ከቤት እንኳ ቢወጣ በፍጥነት ተመልሶ ሊመለስ ይችላል፤ ድመትዎን ቤት ውስጥ ማቆየት ወይም ደኅንነቱ አስተማማኝ በሆነ ሁኔታ ከቤት ውጪ መንቀሳቀስ ይችላል” ይላሉ።

የድመት ባለቤት ከሆኑ ወይም ድመት ማሳደግ የሚሹ ከሆነ ድመትዎን ደስተኛና ጤናማ አድርጎ ለመጠበቅ በአካባቢዎ የሚገኘውን የእንሰሳት ሕክምና መስጫ ይጎብኙ።

“የእንሰሳት ሕክምና መስጫ የእያንዳንዱ የድመት ባለቤት የድመት ጤና ቀዳሚ መረጃ ማግኛ መሆን ይገባዋል። ዓመታዊ የጤና ምርመራ፣ ክትባቶችና ማናቸውም ዓይነት አስፈላጊ የሕክምና እቅዶችን እንሰሳዎ ማግኘት እንዲችል የእንሰሳት ሐኪም ፈልገው ማግኘት ይኖርበታል። ሁሌም በተቻለ ፍጥነት ሕመምን አስመርምሮ ማግኘትና ተገቢውን ሕክምና ማስደረግ ከእንሰሳ ሐኪሞ ጋር ማለፊያ ግንኙነት መመሥረቻ መልካሙ መንገድ ነው" ሲሉ የእንሰሳት ሐኪምና የአውስትራሊያ የእንሰሳት ሐኪሞች ማኅበር የምዕራብ አውስትራሊያ ቅርንጫፍ ፕሬዚደንት ጋርኔት ሆል ይመክራሉ።

ከቤት ውጪ የሚዘዋወሩ ለማዳ ድመቶች የዱር ሕይወትን አድነው የሚያጠፉ ብቻ ሳይሆኑ እራሳቸውም ለሕመም ወይም ለመቁሰል አደጋ ተጋላጭ እንደሚሆኑ ዶ/ር ሆል አክለው ሲያሳስቡ፤

“ድመቶች በአብዛኛው እርስ በርሳቸው ይጣላሉ። ብርቱ የሆነ ቁስልን ያስከትላሉ፤ እንዲሁም እንደ FIV ለመሳሰሉ በሽታዎችና ለመኪና አደጋዎች በእጅጉ ተጋላጭ ይሆናሉ። ድመቶች በተፈጥሯቸው ገዳዮች ናቸው፤ ይህንንም በአጨዋወት ባሕሪያቸው ሲያንፀባርቁት እናያለን። ማሳደድ፣ መወዝወዝና መናከስን ይወዳሉ። ከቤት ውጪ ባለ ሁኔታ እነዚህ ባህሪዮች በፍጥነት ወደ ገዳይ እደና ይለወጣሉ” ብለዋል።
SG CAT Ownership 5.jpg
Impacts of urban cats in Australia. Threatened Species Recovery Hub. Note the estimate of the pet cat population shown in this poster (4.9 million) has been surpassed; recent surveys put the figure at 5.3 million.

ድመቶችን እንደ ቤት ውስጥ እንሰሳት ለማሳደግ የአካባቢ ሕጎች ምን ይመስላሉ?

ፕሮፌሰር ሌጌ፤ አውስትራሊያ ውስጥ ድመትን የማሳደግ ሕጎች እንደሚኖሩበት አካባቢ የተለያዩ መሆኑን አንስተው ይናገራሉ።

“የድመት አስተዳደር ሕጎች በክፍለ አገራትና ግዛቶች የተደነገጉ ናቸው። ይሁንና ግብር ላይ አዋዋሉ በአካባቢ መንግሥታት ይወሰናል። እንዲሁም፤ የአካባቢ መንግሥታት የራሳቸውን ተጨማሪ ሕጎች ማውጣት ይችላሉ። የአካባቢ መንግሥታት ለምሳሌ ያህል ሁሉም ድመቶች እንዲኮላሹ ወይም ሁሉም በተወሰኑ ክፍለ ከተማ ያሉ ድመቶች በጥብቅ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ የሚሉ ሕጎችን ማውጣት ይችላሉ። እናም ያ ማለት ሕጎቹ እንደሚኖሩበት አካባቢ ይለያያል ማለት ነው።"

የቤት ውስት ለማዳ ድመቶችን ማሳደግን አስመልክቶ እርስዎ በሚኖሩበት አካባቢ ያለውን የማዘጋጃ ቤት ድረገፅ ይጎብኙ።

“ሁላችንም ኃላፊነት የተመላበት የእንሰሳት ባለቤትነትን ግብር ላይ ካዋልን በቤት ውስጥ ለማዳ ድመቶቻችን እንደሰታለን ማለት ነው። ስለምን፤ ድንቅ አጫዋቾች ናቸው፣ በተመሳሳይ መልኩም ፌሪሬን ወፎችን፣ ትናንሽዬዎቹን እንሽላሊቶችና ሁሉንም የጓሮ አትክልቶቻችንን የሚጎበኙትን የዱር ሕይወቶች ሁሉ” በማለት ፕሮፌሰር ሌጌ ምክር ሃሳባቸውን ለግሰዋል።
እንደምን ኃላፊነት የተመላው የቤት ውስጥ ለማዳ ድመት ባለቤት መሆን እንደሚችሉ ተጨማሪ መረጃን ይሻሉ? የአካባቢዎን ማዘጋጃ ቤት ድረገፅና የሚከተሉትን ሊንኮች ይጎብኙ፤

Share