መኪናን በማሽከርከር ላይ እያሉ የሚፈጠር ውዝግብ ምንድን ነው እንዴትስ ማሳለፍ ይቻላል ?

Australia Explained - Road Rage

Credit: Jacobs Stock Photography Ltd/Getty Images

አመጻን የተሞላ የማሽከርከር ባህሪ አደጋ እንዲጨምር እና በጎዳና ላይ የአመጽ ተግባር እንዲጨምር ምክንያት ይሆናል ፡፡በአውስትራሊያ መኪናን እየነዱ አመጽ የሚፈጥሩ ሰዎች ፤ በአብዛኛው የመንገድ ላይ ህጎችን በመጣስ የኢንሹራንስ ሪኮርዳቸውን የሚያበላሹ ፤ እንዲሁም የራሳቸውን እና የሌሎችንም ህይወት አደጋ ላይ የሚጥሉ ናቸው፡፡ ደህንነቱ የተጠበቅ እና ሀላፊነት የሚሰማው የማሽከርከር ልማድን መማር እና ማጎልበት ፤ እንዲሁም እርስዎ ወይም በእርስዎ ዙሪያ ያሉ ወዳጆችዎ በማሽከርከር ላይ እያሉ በሚፈጠር ውዝግብ ሳቢያ አደጋ ከገጠማችሁ ምን ማድረግ እንደሚገባዎት ይማሩ ፡፡


Key Points
  • አመጻን የተሞላ የማሽከርከር ባህሪ እና የጎዳና ላይ አምባጓሮ ከግላዊ እና በአካባቢያችን ዙሪያ ባሉ ምክኛቶች ሊከሰቱ ይችላሉ
  • በማሽከርከር ላይ እያሉ በሚፈጠር ውዝግብ ውስጥ ከገቡ ሁኔታውን ለማጋጋል አይሞክሩ
የመንጃ ፈቃድ ያለው አሽከርካሪ መሆን ማለት ለሌሎች ሀላፊነት የሚሰማዎ አሽከረካሪ እንዲሆኑ ይጠበቅብዎታል፡፡
ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች በቁጣ እና ንዴት ውስጥ ሆነው በሚያሽከረክሩበት ጊዜ የሚወስዱት እርምጃ እና የሚመርጡት ምርጫ ፤ የሌሎችን ህይወት አደጋ ላይ ሊጥሉ የመንገድ ላይ ደህንነትን ሊያቃውሱ ይችላሉ፡፡

ምንም እንኳ በማሽከርከር ላይ እያሉ በሚፈጠር ውዝግብ ሳቢይ የተፈጠረን አደጋን በተመለከት በትክክል የተሰበሰበ አሀዛዊ መረጃ ባይኖርም ፤ በ2024 በ comparison site Finder በተደረገ መጠይቅ ፤ ከአራት አውስትራሊያውያን መካከል ሶስቱ በማሽከርከር ላይ እያሉ በሚፈጠር ውዝግብ አጋጥሟቸዋል፡፡

Australia Explained - Road Rage
Impatient woman gesturing while driving car during rush hour in the city Credit: freemixer/Getty Images
በኩዊንስላድ ዪኒቨሪሲቲ የስነልቡና ትምህርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር ጄምስ ኪርቢ በማሽከርከር ላይ እያሉ በሚፈጠር ውዝግብ ዚሪያ ምርምርን አድርገዋል ፡፡

እንደ እሳቸው አባባል ከሆነ አመጻን የተሞላ የማሽከርከር ባህሪ እና የጎዳና ላይ አምባጓሮ፤ በግለሰቦቹ አመለካከት እና ግትር ባህሪ ፤ እንዲሁም በጾታ እና እድሜ ሳቢያ ሊከሰት ይችላል፡፡
" ለምሳሌ እያሽከረከሩ ሳሉ አንዳንድ ሰዎች ሆነ ብለው በእኔ ላይ ክፉ ነገርን ያደርጋሉ ብሎ ማመን ፤ ለዚህ ጥሩ ምሳሊ የሚሆነውም ሆነ ብለው ቀድመውኝ ሄዱ የሚለውን መጥቀስ እንችላለን ፡፡"

በተጨማሪም በህይወታችን ውስጥ ያለው ጫና ለዚህ አስተዋጽኦ ሊያደርግ ይችላል፡፡

" ሰአት አለፈብኝ ብሎ መጣደፍ ትልቁን ቦታ የሚይዝ ሲሆን ፤ ሰዎች ከአንድ ስፍራ ወደሌላው በጥድፍፊያ የሚጓዙ ከሆነ እና በመንገዳቸው ላይ የትራፊክ ፍሰቱን የሚያደናቅፍ እና የሚያዘገያቸው ነገር ካጋጠማቸው ፤ ይህ አምባጓሮ ውስጥ እንዲገቡ ሊገፋፋቸው ይችላል ፡፡"

በማሽከርከር ላይ እያሉ የሚፈጠር ውዝግብ እና አምባጓሮ ድህንነቱ ያልተጠበቀ የማሽከርከር ዝንባሌን ፤ ራስን መቆጣጠር አለመቻልን ያስከትላል ፡፡
" በንዴት ውስጥ ስንሆን ሙሉ ትኩረታችንን የምናደርገው ንዴቱን በፈጠረብን ሰው ዙሪያ ነው ፡፡ በዚህም መሰረት ይህ ቀረ የሚይባል እና ከማንም የምንበልጥ አሽከርካሪዎች ነን ብለን የተሳሳተ አስተሳሰብን እናዳብራለን ፡፡ይህም ለተጨማሪ ውዝግብ እና የአደገኛ አሽከርካሪ ባህሪ እንዲኖረን ያደርጋል ፡፡ " ሲሉ ፕሮፌሰር ኪልቢ ያስረዳሉ ፡፡

" ስለዚህ ከሌሎች የበለጠ የማሽከርከር ችሎታ አለን ብሎ ማመን ይህ ግልጽ ችግር ነው ፡፡"
Australia Explained - Road Rage
Angry Middle Eastern man Attacking Another Driver Sitting In Car Credit: DjelicS/Getty Images
መኪናን በማሽከርከር ላይ እያሉ የሚፈጠር አምባጓሮን እንዴት መከላከል ይቻላል ፡፡

በዋናነት ከሚጠቀሱት እና መኪናን በማሽከርከ ላይ እያሉ ለሚፈጠሩ አምባጓሮዎ መንሳኤዎች ከሚባሉት ውስጥም ሌላውን ሰው ለማበሳጨት ሆነ ብሎ ያልተጠበቀ ፍሬን መያዝ ፤ሎላኛውን መኪና ተጠግቶ መንዳት ፤ ከመጠን በላይ የሚደረግ ፍጥነት ፤ ሌላኛው አሽከርካሪ ከስፍራው እንዲለቅ መብራትን ብልጭ ድርግም ማድረግ የሚሉት በዋነኛነት ተጠቃሾች ናቸው፡፡

በቪክቶሪያ በእንዲህ አይነት ባህሪያት ሳቢያ ለሚፈጠሩ አደጋዎች በየአመቱ 2000 ቅጣቶች ይሰጣሉ ፡፡

" የቪክቶርያ ሮያል አውቶሞቢል ክለብ የፖሊሲ ሃላፊ ጄምስ ዊሊያምስ እንደሚሉት " በሁለት መኪናዎች መካከል ሊኖር የሚገባን ርቀት በሴንቲ ሜትር የመለካት ነገር አይደለም ፤ ቁም ነገሩ ይህ ለምን ይደረጋል አላማው ምንድን ነው የሚለውን ማየቱ ላይ ነው፡፡"

" ረዘም ላለ ጊዜ ከፊት ለፊትዎ ያለውን መኪና በጣም ተጠግተው ሲቆዩ ፤ ተመጣጣኝ የሆነን ስፍራን እንዲተዉ የሚያዘውን ህግ በመጣስ ሊያስጠይቅዎ ይችላል ፡፡"
Angry Woman Gestures in Car
Road rage in itself is an offence, however actions associated with aggressive driving compromising road safety are penalised. Credit: John W. Banagan/Getty Images
.
እያሽከረከሩ ሳለ ራስዎን በዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ካገኙ ለደህንነትዎ ቅድሚያን ሊሰጡ ይገባል ፡፡

“አሽከርካሪ እየተከታተለኝ ነው ብለው ካመኑ ፤ ክብረ ነክ የሆኑ ቃላቶች ከተሰነዘሩ እና ጥቃቶች ከተፈጸሙ ፤ በእንዲህ አይነት አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ራስዎን ካገኙት እና ላማሽከርከር ከተቸገሩ ፤ ደህንነትዎ ሊጠበቅ ወደ ሚችልበት ቦታ መኪናዎትን በማቆም በአስቸኳይ ለፓሊስ መደወል ይኖርብዎታል ፡፡ "

ከመጀመሪያው እስከመጨራሻው ሊፈታተንዎት ከሚችል አሽከርካሪ ጋር ራስዎን ካገኙት ፤ በተቻለዎት መጠን ራስዎን በማረጋጋት ደህንነትዎ ሊጠበቅ ወደሚችልበት ቦታ መኪናዎን ዞር አድርጎ በማቆም ሌላኛው አሽከርካሪ እንዲያልፍዎ ያድርጉ ፡፡

ሚስተር ዊልያም አያይዘውም ' በምንም አይነት መልኩ ተጨማሪ የሆነ የባላንጣነትን ወይም ነገር በሚያባብስ ሁሌታ ውስጥ ራስዎን መክተት እንደሌለብዎት ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡"

መኪናን በማሽከርከር ላይ ስለሚፈጠር ውዝግብ እና ኢንሹራንስ

እንደሚታወቀው የመኪና ኢንሹራንስ መኪናን በማሽከርከር ላይ እንዳሉ በተፈጠረ አምባጓሮ ወይም አደጋ ለደረሰ ጉዳት ክፍያል ይፈጽማል ፡፡
የፍሊንደር ኢንሹራንስ ባለሙያ የሆኑት ቲም በኔት እንደሚሉት አብዛኛውን ጊዜ ኢንሹራንሱን የሚከፍሉት ችግሩን የፈጠሩት አሽከርካሪዎች ኢንሹራንስ ድርጅት ነው ፡፡

" ሁለቱ መኪናዎች ቆመም መረጃዎችን መለዋወጥ ይኖርባቸዋል፡፡ "
ይህ ሁል ጊዜም በቀላሉ የማይቻል ሊሆን ይችላል ፤ በተለይ አንደኛው ወገን አመጸኛ ከሆነ ማለት ነው፡፡ ስለሆነም በተቻለዎት ፍጥነት እያንዳንዱ መረጃ በትክክል ዘግበው ይያዙ ፡፡ እንዲሁም የታርጋ ቁጥሩን መዝግበው ለመያዝ ይሞክሩ፡፡ "
Australia Explained - Road Rage
Cyclists and pedestrians are road users who are also potential targets of road rage behaviours. Credit: olaser/Getty Images
በማሽከርከር ላይ እያሉ በሚፈጠር ውዝግብ ሳቢያም አደጋ ከተከሰተ ፤ ችግሩን ፈጣሪው በኢንሹራንስ ድርጅቱ በኩል የሚጣልበትን መቀበል ይኖርበታል ፡፡

በእርስዎ ምክንያት አደጋ ከተፈጠረ እና የእርስዎ ኢንሹራንስ ድርጅት ክፍያውን ከፈጸመ ፤ አመታዊ የኢንሹራንስ ክፍያዎ መጨመሩ የማይቀር እና ትክክልም ነው ፡፡


እኔ ተሳፋሪ ከሆንኩኝስ ?

ተሳፋሪ ሆነው ሳሉ በመኪናው ውስጥ የሚፈጠር ውዝግብ በእርስዎ ላይ የሚያስከትልብዎት ፍርሀት እና ጭንቀት አለ፡፡

ፕሮፌሰር ኪቢ ይህ ለምን ሊሆን እንደሚችል ሲያስረጉ

" በዚህ ሁኔታ ውሽጥ የሚሰማዎት አቅም ማጣትን ነው ፤ በተጫማሪም እንደ አመጻው ሁኔታ ህይወትዎ አደጋ ውስጥ ሊሆን ይችልም ይሆናል ፡፡"

ነገሩን ለማብረድ ጥረት ካደረጉ ለምሳሌ 'ተረጋጉ ' የሚለውን ቃልን ከተጠቀሙ ፤ በአብዛኛው ከሌላኛው ወገን አወንታዊ ምላሽን ሊያስገኝ ይችላል ፡፡ በተቃራኒው ይህ አባባልን በተቃራኒው መንገድ ሊወስዱ የሚችሉ እና ቀይ መስመርን እንዳለፉ ተደርጎ ሊቆጠርብዎት ይችላል፡፡ "

Australia Explained - Road Rage
You can try several strategies as a passenger to calm down the driver amidst a road age incident, but their effectiveness will depend on the nature and quality of your relationship. Credit: PixelsEffect/Getty Images

Australia Explained - Road Rage
If a person consistently engages in road rage behaviour, psychological therapy can help them deal with the management and expression of their anger, Prof Kirby says. Source: Moment RF / Fiordaliso/Getty Images
If you feel unsafe amidst a road incident, contact the police.

Bad driving behaviour can also be reported by calling Crimestoppers on 1800 333 000.

Share